በዓለም ትልቁ የእድሜ ባለጸጋ ልደታቸው ከመድረሱ ከ2 ወራት በፊት ህይወታቸው አለፈ
ሁለቱን የዓለም ጦርነቶች እና የኮሮና ወረረሽን ያሳለፉት ፔሬዝ ከኢዲዮፊና ዴል ሮዛሪዎ ግራሻ ጋር እስከሞቱበት 1997 ደረስ በትዳር ለ60 አመታት ያህል ኖረዋል
የዓለም የእድሜ ባለጸጋው ሰው 115ኛ አመት የልደት ቀናቸው ከመድረሱ ከሁለት ወራት በፊት ህይወታቸው አልፏል
በዓለም ትልቁ የእድሜ ባለጸጋ ልደታቸው ከመድረሱ ከ2 ወራት በፊት ህይወታቸው አለፈ።
የዓለም የእድሜ ባለጸጋው ሰው 115ኛ አመት የልደት ቀናቸው ከመድረሱ ከሁለት ወራት በፊት ህይወታቸው ማለፉን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
በ114 አመታቸው በዚህ ሳምንት ህይወታቸው ያለፈው ጁአን ቪሰንት ፔሬዝ የተባሉት ቬንዝዌላዊ ግለሰብ የዓለም ትልቁ የእድሜ ባለጸጋ መሆናቸው በጊኒየስ ወርድ ሪከርድስ የተረጋገጠው በ2022፣ 112 አመት ከ253 ቀናት ሲሞላቸው ነበር።
ሁለቱን የዓለም ጦርነቶች እና የኮሮና ወረረሽን ያሳለፉት ፔሬዝ ከኢዲዮፊና ዴል ሮዛሪዎ ግራሻ ጋር እስከሞቱበት 1997 ደረስ በትዳር ለ60 አመታት ያህል ኖረዋል።
በ1909 የተወለዱት ፔሬዝ ረጅም እድሜ እንዲኖሩ ያስቻላቸው "ጠንክሮ መስራት፣ በበዓል ቀን እረፍት መውሰድ፣ ቀደም ብሎ መተኛት፣ አንድ ብርጭቆ አልኮል መጠጣት እና ፈጣሪን መውደድ ነው" ይላሉ።
ፔሬዝ ከባለቤታቸው ግራሽያ ስድስት ወንድ እና አምስት ሴቶችን ጨምሮ 11 ልጆችን አፍርተዋል። ጥንዶቹ ቆይተው 11 የልጅ ልጆች እና 12 የልጅ ልጅ ልጆች ለማየት በቅተዋል።
በ2019 ፔሬዝ ከ100 አመት በላይ የሆናቸው የመጀመሪያው ቬንዝዌላዊ ተብለው 110 አመታቸውን አክብረዋል።
ፔሬዝ የኖሩበት ታቺራ ግዛት አስተዳዳሪ የሆኑት ፍሬዲ በርናል በትዊተር ገጻቸው" ወድ ጁአን ቪሰንት ፔሬዝ በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ሆነን እንሰናበትሀለን" ሲሉ ጽፈዋል።
ፔሬዝ የመልካምነት፣ የጥበብ እና የደስታ ምንጭ እንነበሩ የገለጹት አስተዳዳሪው አሻራቸው ምንጊዜም በልባችን ይኖራል ብለዋል።
የፔንዝዌላው ፕሬዝደንት ኒኮላስ ማዱሮ ፔሬዝ የእድሜ ባለጸጋው ቬንዙዌላን በጊኒየስ ሪከርድ አመዝግቧል ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ለፔሬዝ ቤተሰቦች እና የትውልድ ቦታቸው ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።