የዓለማችን ባለጸጋዎች ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ 40 ትሪሊዮን ዶላር ማትረፋቸው ተገለጸ
ትርፉን ያገኙት ባለጸጋዎች ከዓለማችን ጠቅላላ ህዝብ ውስጥ የ1 በመቶ ድርሻ ያላቸው ናቸው
ባለጸጋዎቹ የከፈሉት ግብር ከትርፋቸው አንድ በመቶ በታች ነው ተብሏል
የዓለማችን ባጸጋዎች ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ 40 ትሪሊዮን ዶላር ማትረፋቸው ተገለጸ፡፡
ዓለማችን አሁን ላይ ያላት ጠቅላላ ህዝብ 7 ነጥብ 9 ቢሊዮን ሲሆን የዚህ ህዝብ አንድ በመቶ ያህሉ ያላቸው ሀብት ከተቀረው 99 በመቶ ህዝብ ጋር ሲነጻጸር በ36 እጥፍ ይበልጣል፡፡
ኦክስፋም የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ባወጣው ጥናት መሰረት ከዓለማችን ጠቅላላ ህዝብ ውስጥ የ1 በመቶ ድርሻ ያላቸው ባለጸጋዎች ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ 40 ትሪሊዮን ዶላር ትርፍ አግኝተዋል ብሏል፡፡
እነዚህ ቅንጡ ባለጸጋዎች ከሚያገኙት ትርፍ ላይ የከፈሉት ትርፍ ከአንድ በመቶ በታች እንደሆነም ተቋም በጥናቱ ለይ ጠቅሷል፡፡
የተሻለ ኢኮኖሚ ያላቸው በተለምዶ ቡድን 20 ሀገራት የፋይናንስ ሚኒስትሮች በብራዚሏ ሪዮ ዲጀነሪዮ ዛሬ እና ነገ ይሰበሰባሉ፡፡
ድል ባለ ሰርግ የተጋቡት የ100 እና የ96 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ጥንዶች
በዚህ ጉባኤ ላይ ዋነኛ መወያያ ይሆናል በሚል የተያዘው አጀንዳ ለዓለም የሀብት አለመመጣጠን ዋነኛ ምክንያት የሆኑት እነዚህ ቅንጡ ባለጸጋዎች ተገቢውን ግብር ግብር እየከፈሉ ባለመሆኑ ተጨማሪ ግብር የሚከፍሉበት ስርዓት ይመቻች የሚለው ነው፡፡
የጉባኤው አስተናጋጅ ብራዚልን ጨምሮ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኮሎምቢያ እና የአፍሪካ ህብረት በባለጸጋዎቹ ላይ የሚጣለው ግብር እንዲጨምር ይፈልጋሉ ተብሏል፡፡
አሜሪካ በበኩሏ በባለጸጋዎቹ ለይ ሊጨመር የታሰበው ግብር ላይ ተቃውሞ እንዳላት የተገለጸ ሲሆን በዚህ ጉባኤ ላይ ላይስማሙ እንደሚችሉ ተሰግቷል፡፡
በዓለማችን ካሉ ቅንጡ ባለጸጋዎች መካከል ከአምስቱ አራቱ በቡድን 20 አባል ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ናቸውም ተብሏል፡፡
በነዚህ ባለጸጋዎች ላይ ሊጣል የታሰበው ግብር ስምንት በመቶ ሲሆን ባለጸጋዎቹ ተገቢውን ግብር ባለመክፈላቸው ምክንያት በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ህይወት ቁጥር እንዲያሻቅብ እያደረገው እንደሆነ ተገልጿል፡፡