ኢኮኖሚ
የዓለማችን ምርጥ 10 አበባ አምራች ሀገራት እነማን ናቸው?
ኔዘርላንድ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ አበባ ከሚያመርቱ የዓለማችን ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/13/258-172626--6-_167adf30250136_700x400.jpg)
የአበባ ኢንቨስትመንት በዓመት ከ40 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ይንቀሳቀስበታል ተብሏል
የዓለማችን ምርጥ 10 አበባ አምራች ሀገራት እነማን ናቸው?
በበለጸጉ ሀገራት ሰፊ የገበያ ድርሻ ካላቸው ምርቶች መካከል አበባ አንዱ ነው።
በተለይም ነገ የሚከበረው የፍቅረኛሞች ቀን ዋነኛ የአበባ ግብይት ከሚፋጸምባቸው ቀናት መካከል ዋነኛው ነው።
የዓለማችን ቁጥር አንድ አበባ ላኪ እና አምራች የሆነችው ኔዘርላንድ ከአበባ ንግድ ብቻ ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ታገኛለች።
የላቲን አሜሪካዋ ኮሎምቢያ ሁለተኛዋ አበባ አምራች ሀገር ስትሆን በዓመት 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ታገኛለች ተብሏል።
ሌላኛዋ የላቲን አሜሪካ ሀገር ኢኳዶር በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ ስታገኝ ከአፍሪካ አንደኛ አበባ አምራች የሆነችው ኬንያ ደግሞ 655 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ታገኛለች
ኢትዮጵያ አበባ ለዓለም ገበያ ከሚያቀርቡ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በዓመት ከ250 ሚሊዮን በላይ ዶላር ገቢ እንደምታገኝ የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።
የአበባ ንግድ በዓመት ከ40 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ኢንቨስትመንት እንደሆነም ተገልጿል።