በግራም 62 ትሪሊየን ዶላር የሚያወጣው የምድራችን ውዱ ንጥረ ነገር
ንጥረ ነገሩ እንደሌሎች ውድ ማዕድናት ከመሬት ውስጥ ተቆፍሮ የሚወጣ ሳይሆን ቅንጣት በቅንጣት የሚገነባ ነው ተብሏል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/18/243-142629-images-4-_700x400.jpeg)
እጅግ ልዩ የሆነው ንጥረ ነገር በአጽናፈ ሰማይ ውስጥ በጥቂት ስፍራዎች በትንሽ መጠን እንደሚገኝ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል
የአለማችን ውድ ማዕድናትን ዋጋ የሚያስንቀው የምድራችን እጅግ ውዱ ንጥረ ነገር በግራም 62 ትሪሊየን ዶላር ዋጋ ተቆርጦለታል፡፡
ከቅንጣቶች ስብስብ እንደሚገነበ የተነገረለት ንጥረ ነገር ለአቶሚክ ሀይል፣ ለህዋ ሳይንስ እና ለኢነርጂ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው ነው የተሰማው፡፡
በአለም ላይ ከፍተኛ ዋጋ እንደወጣላቸው እንቁዎች ፣ ንጥረነገሮች ፣ ወርቅ፣ የብረት አይነቶች እና ሌሎችም ማዕድናት ይህን ንጥረ ነገር ከመሬት ወይም ከውሀ ውስጥ ቆፍሮ ማግኝት አይቻልም፡፡
ይህን በአጽናፈ ሰማይ (ዩኒቨርስ) ውስጥ በጥቂት መጠን የሚገኘውን ንጥረ ነገር ለመግዛት ገንዘቡ ቢኖሮዎት እንኳን ቅንጣቶች ተሰባስበው አንድ ግራም ተሰርቶ እስኪያልቅ ድረስ ቢሊየን አመታትን መጠበቅ ሊኖርብዎት እንደሚችል የደይሊሜል ዘገባ ያስረዳል፡፡
ምንም እንኳን ነገሩ ከሳይንስ ልብወለድ የወጣ ነገር ቢመስልም የአተሞች ጸረ ቁስአካል (አንቲማተር) በምድር ላይ ካሉት እጅግ በጣም ጠቃሚ እና ውድ ቁሶች መካከል እንደሆኑ ይታመናል።
ቁስ አካል እና ጸረ ቁስአካል ሲገናኙ እርስበእርሳቸው በሚፈጥሩት ግጭት ይህን ከፍተኛ ዋጋ የወጣለትን ንጥረ ነገር እንደሚያስገኙ ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡
ግጭቱ በሚፈጠርበት ጊዜ ጸረ ቁስአካል ወዲያውኑ የሚጠፋ ከመሆኑ የተነሳ ለማከማቸት እና ለማጥናት ሁኔታዎች አስቸጋሪ በመሆናቸው የንጥረ ነገሩ ዋጋ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ሁሉም ቅንጣቶች ፣ ፕሮቶንስ፣ ኒውትሮንስ ፣ ኤሌክትሮንስ እና የሰብአቶሚክ ቅንጣቶች የሚታየውን ዩኒቨርስ በመፍጠር ትልቅ ሚና ሲኖራቸው ከዚህ ባለፈ እርስ በእርሳቸው በሚፈጥሩት ውህደት የሚያስገኙት ሀይል (ኢነርጂ ) በመጠኑ ከፍተኛ ነው፡፡
እ.ኤ.አ. በ1999 የናሳ ተመራማሪ ሃሮልድ ጌሪሽ የጸረ ቁስ አካል (አንቲማተር) ዋጋ 62.5 ትሪሊዮን ዶላር ሊሆን እንደሚችል አስቀምጦ ነበር፡፡
በሲኢአርኤን የፊዚክስ ሊቅ የሆኑት ፕሮፌሰር ማይክል ዶዘር በአንድ አመት ውስጥ የምንሰራው ቁስ አካል አንድ ኩባያ ሻይ እንኳን ለማፍላት በቂ አይደለም ይላሉ፡፡
በዩኒቨርስ ውስጥ ቁስአካል እና ጸረ ቁስ አካል በሚፈጥሩት ግጭት የሚፈጠረውን ንጥረ ነገር በግራም መጠን ለመሰብሰብ ከሚወስደው እጅግ ረጅም አመት ጋር ተያይዞ ይህን ውህደት ከዚህ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማግኝት የሚቻልበት ሳይንሳዊ ዘዴ ከተፈጠረ ታሪክ ቀያሪ እንደሚሆንም አስረድተዋል፡፡
62 ትሪሊየን ዶላር የወጣለትን ንጥረ ነገር አንድ ግራም እንኳን ማሰባሰብ ቢቻል በአቶሚክ እነርጂ፣ በመንኮራኩር ሀይል እና በሌሎችም የሀይል ዘርፎች የሚፈጥረው ልዩነት ከሚገመተው በላይ ሀይለኛ እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡