በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተሰራጩ ቦምቦች በመላው አውሮፓ አሳሳቢ ሆነዋል ተብሏል
በእንግሊዝ ግሬት ያርማውዝ 250 ኪሎ ግራም የሚመዝን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ቦምብ ባልተጠበቀ ሁኔታ መፈንዳቱን ፖሊስ አስታውቋል።
ባለፈው ማክሰኞ በወንዝ ማቋረጫ ላይ ትልቅ ያልተፈነዳ መሳሪያ መገኘቱን ተከትሎ የአደጋ ሰራተኞች ለማምከን ሲሰሩ ቆይተዋል።
ሆኖም አርብ ከሰአት በኋላ መሳሪያው ሳይታሰብ እንደፈነዳ ተናግሯል። በፍንዳታው ምንም ሰው አልተጎዳም ነው የተባለው።
የሀገሪቱ ጦር ባለሞያዎች ቦምቡን ቀስ ብሎ በማቃጠል ፈንጂዎቹን ለማምከን እየቆረጡት ነበር ተብሏል። ሆኖም መሳሪያው በቁጥጥር ላይውል ይችላል የሚል ስጋት እንደነበር ተገልጿል።
መሳሪያውን ለማምከን የመቁረጥ ስራ ተጀምሮ ነበር የተባለ ሲሆን፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልገው ውሃ በመሳሪያው ዙሪያ ያለውን የአሸዋ መከላከያ ውጤታማነት እንደቀነሰው ተነግሯል።
መሳሪያው አንድ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ወደ 250 ኪሎ ግራም ይመዝናል ተብሏል።
ያሬ በተባለ ወንዝ ላይ በስራ ተቋራጭ መገኘቱን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያልተፈነዱ ቦምቦች በመላው አውሮፓ ማለት አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል ተብሏል።