“ቆሻሻው/ደርቲ ቦምብ” በመባል የሚጠራው የቦምብ አይነት ምንድን ነው?
ሩሲያ ከሰሞኑ በደተጋጋሚ ዩክሬን “ቆሻሻውን ቦምብ” ልትጠቀም ትችላች እያለች ስጋቷነን እየገለጸች ነው
ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘው “ቆሻሻው ቦምብ” ለሰዎች ጤና ጠንቅ እንደሆነ ይነገራል
ሩሲያ ከሰሞኑ “ዩክሬን ቆሻሻውን ቦምብ (ደርቲ ቦምብ) ለመጠቀም አቅዳለች” ስትል ስጋቷን እየገለጸች መሆኑ ይታወቃል
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ "ኪየቭ የቆሻሻ ቦምብንን ለመጠቀምን አያደረገች ያለው እንቅሰቃሴ ሀገራቸውን እንዳሳሰበ መናገራቸውም ይታወሳል።
ዩክሬን በበኩሏ “ቆሻሻውን ቦምብ” ልትጠቀም ትችላለች በሚል የቀረበባትን ከስ ውድቅ ያደረተች ሲሆን፤ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካም የሩሲያን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል።
“ቆሻሻው ቦምብ” ምንድን ነው?
“ቆሻሻው ቦምብ” ዩራኒየም ያሉ ሬዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘ ቦምብ ሲሆን፤ በሚፈነዳበት ጊዜ የአካባቢ የአር ላይ በመበተን አየርን የሚበክል መሆኑ ይነገራል።
ቆሻሻው ቦምብ በኒውክሌር ቦምብ ውስጥ ጥቅም ላይ እንደሚውለው በጣም የተጣራ ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር ነገሮችን በውስጡ አይዝም፤ ይልቁንም ከሆስፒታሎች፣ ከኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ወይም ከምርምር ላቦራቶሪዎች የሚገኙ ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር ነገሮችን በመጠቀም ጊዜን እና ወጪን በቆጠበ መልኩ በቀላሉ የሚሰራ የቦምብ አይነት ነው።
ቆሻሻው ቦምብ በቀላሉ በመኪና ጀርባ ላይ በሚጫን ማስወንጨፊያ አማካኝነት የሚተኩስ መሆኑንመ ነው የሚነገረው።
“ቆሻሻው ቦምብ” ምን አይነት የጤና እክል ያስከትላል?
ከቆሸሸ ቦምብ ዋናው አደጋ ከፍንዳታው በኋላ በሰዎች ላይ የሚደርስ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት መሆኑ ይታወቃል።
በቆሸሸ ቦምብ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉት ራዲዮአክቲቭ ቁሶች ምናልባት ፍንዳታው ከሚከሰትበት ቦታ በጣም ቅርብ ከሆኑ ሰዎች በስተቀር ለአፋጣኝ ከባድ ሕመም የሚዳርግ በቂ የጨረር መጋለጥ አይፈጥርም።
ሆኖም ግን በቦምቡ ውስጥ የሚገኘው የራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር በአቧራ እና ጭስ መልክ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በአየር ላይ ተበትኖ ሰዎች ሲተነፍሱ ወደ ውስጥ ከገባ ለጤና አደገኛ ሊሆን እንደሚችልም ነው የሚነገረው።
ቆሻሻው ቦምብ በዚህ መልኩ በሰዎች ላይ ከሚያስከትላቸው የጤና እክሎች ውስጥ የካንሰር ህመም አንዱ እንደሆንም ይነገራል።
በዚህም ምክንያት ቆሻሻው ቦምብ በህዝብ ዘንድ የሽበር መፍጠሪያ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን፤ እንደ ጦር መሳሪያ ግን በጣም አስተማማኝ አይደለም።