ተሸላሚዎቹ በ1945 በጃፓኗ ኦኪናዋ 31 ወታደሮችን የጫነ አውሮፕላን ለማረፍ ሲሞክር ተከስክሶ ህይወታቸው ያለፉ ናቸው
አሜሪካ ከ80 ዓመት በፊት ለሞቱ ወታደሮች የጀግና ሽልማት ሰጠች፡፡
ሁለተኛው ዓለም ጦርነትን ዘግይታ የተቀላቀለችው አሜሪካ ጦርነቱን በበላይነት ካጠናቀቁ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ናት፡፡
በዚህ ጦርነት አሜሪካ እና አጋሮቿ አሸናፊ እንዲሆኑ የጃፓን ዝርያ ያላቸው አሜሪካዊያን ድርሻ ቀላል አልነበረም፡፡
እነዚህ ወታደሮች በተለይም ጃፓንኛ ቋንቋን በመተርጎም፣ ጃፓንን በመሰለል እና ሌሎች ወታደራዊ ግዳጆችን እንደፈጸሙ ገለጻል፡፡
ጃፓን በዚህ ጦርነት ከተሸነፈች በኋላ ለተጨማሪ ወታደራዊ ስራዎች ወደ ጃፓኗ ኦኪናዋ በአውሮፕላን ያመሩ 31 ወታደሮች በገጠማቸው አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡
አሜሪካ በዚህ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ለተሳተፉ ወታደሮች የጀግና ሜዳሊያ የሸለመች ቢሆንም በኦኪናዋ ወታደራዊ አውሮፕላን ውስጥ ከተሳፈሩ እና በአደጋ ምክንያት ከሞቱ 31 ወታደሮች መካከል ሁለቱን ብቻ ሸልማም ነበር፡፡
አሜሪካ የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል ገድየዋለሁ ያለችው ሰው ድሃ ገበሬ ሆኖ ተገኘ
ይህ ክስተት ከተፈጠረ 80 ዓመት በኋላም ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና መስጠቷን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ለእነዚህ ወታደሮች የጀግና ሜዳሊያ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ሽልማቱም የሟች ወታደሮች ቤተሰቦች ተሰጥቷል፡፡
ይህን የጀግና ሽልማት የወሰዱት የአራት ወታደሮች ቤተሰቦች ሲሆኑ የቀሪ ወታደሮች ቤተሰቦች እየተፈለጉ እንደሆነም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ክስተቱ ከተፈጠረ ረጅም ጊዜ ማስቆጠሩን ተከትሎ በአደጋው የሞቱ ወታደሮች ቤተሰቦችን በቀላሉ ማግኘት እንዳልተቻለ የተገለጸ ሲሆን የሟች ቤተሰቦች ሲመጡ ሜዳሊውን መውሰድ ይችላሉም ተብሏል፡፡