የኤክስ ባለቤት ኢለን መስክ እንዲህ አይነት አቅድ ወደ ተግባር ያስገባል የሚል አሉባልታ ለወራት ሲወራ ቆይቷል
ኤክስ የቆዩ እና አገልግሎት ያቆሙ አካውንቶችን ሊሸጥ መሆኑ ተነገረ።
የኤክስ ማህበራዊ ሚዲያ ወይም የቀድሞው ትዊተር የቆዩ እና አገልግሎት መስጠት ያቆሙ አካውንቶችን ለመሸጥ በሂት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
እንደመረጃው ከሆነ ኤክስ አንዱን አካውንት በ50ሺ ዶላር ለመሸጥ አስቧል።
ይህ ባለፈው አመት እንደተጀመረ የተገለጸው እንቅስቃሴ ጎልቶ የወጣው የሽያጭ ጥያቄዎች ሊገዙ ይችላሉ ለተባሉ ሰዎች የኢሜል መልእክት ከደረሰ በኋላ ነው።
ፎርቦስ መጽሄት ያገኘው የኤክስ ኢሜል እንደሚያሳየው በኩባንያው ውስጥ ያለ 'አትሀንድል' የተባለ ቡድን በተጠቃሚዎች የተተው አካውንቶችን ለመሸጥ ገበያ ፈጥሯል።
ኤክስ የመግዛት አቅም አላቸው ብሎ ለሚያስባቸው ሰዎች 50ሺ ዶላር ግዙ የሚል የኢሜል መልእክት የሚልክባቸው አጋጣሚዎችም አሉ ተብሏል።
ፎርስ የተቀባዮችን ደህንነት ለመጠበቅ በማሰብ ለማን እንደተላኩ ሙሉ በሙሉ ያልገለጻቸው እነዚህ የኢሜል መልእክቶች የተላኩት ከኩባንያው ስራተኞች ነው።
ኩባንያው በሚሸጥበት 'ሀንድል' ላይ ያሉ ደንብ እና መመሪያዎችንም አሻሽሏል።
የኤክስ ባለቤት ኢለን መስክ እንዲህ አይነት አቅድ ወደ ተግባር ያስገባል የሚል አሉባልታ ለወራት ሲወራ ቆይቷል።
መስክ በፈረንጆቹ 2022 በመጀመሪያ ላይ በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ብዙ ቁጥር ያላቸው አካውንቶችን መሰብሰቡን እና የአርትኦት ስራ እንደሚሰራባቸው መግለጹ ይታወሳል።
የኤክስ 'ኢንአክቲቭ አካውንት ፖሊሲ' እንደሚለው ከሆነ ተጠቃሚዎች 'ኢንአክቲቭ' ተደርገው እንዳይቆጠሩ በየ30 ቀናቱ ወደ አካውንታቸው መግባት ይጠቅባቸዋል።
ኤክስ በአሁኑ ወቅት 'ኢንአክቲቭ' የሆኑ አካውንቶችን ዝርዝር አለቀቀም።