“ዜኖቦትስ” የሚባሉት ሮቦቶቹ ህይወት ካላቸው ህዋሶች የተሰሩ ናቸው
የሳይንሱ ዓለም በየእለቱ አዳዲስ ግኝቶችን እያሰማን ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊራቡ የሚችሉ ሕይወት ያላቸው ሮቦቶችን መፍጠር መቻሉን አሰምቶናል።
ሊራቡ ይችላሉ የተባሉት ሮቦቶቹ “ዜኖቦትስ” የሚል መጠሪያ ያላቸው ሲሆን፤ ተመራማሪዎች ህይወት ካሏቸው ህዋሶች እንደሰሯቸው ተነግሯል።
አዲስ የተሰሩት “ዜኖቦትስ” ሮቦቶች ልክ እንደሌሎች ሮቦቶች የተሰጣቸውን ተልእኮ በአግባቡ የሚፈጽሙ ናቸው የተበለ ሲሆን፤ ከሌሎች ለየት የሚያደርጋቸው ደግሞ መራባት መቻላቸው ነው።
ሆኖም ግን “ዜኖቦትስ” ሮቦቶች የሚራቡበት መንገድ ሌሎች ህይወት ያላቸው ፍጥረታት ከሚራቡበት መንገድ የተለየ እንደሆነም ነው ተመራማሪዎች ያስተወቁት።
ዜኖቦት ሮቦቶች ጥፍር ካላቸው የአፍሪካ እንቁራሪት ሽሎች የተገኙ የቆዳ ሴሎችንና የልብ ጡንቻ ሴሎች በመቀላቀል እንደተፈጠሩ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።
ዕቃዎችን መሸከም እና መግፋት የመሳሰሉ ተግባራትን ያሉ ተግባራትን እንዲከውኑ ታስበው የተሰሩት ሮቦቶቹ በኋላ ላይ ግን ራሳቸውን ማባዛት ሁሉ እንደሚችሉ ለማወቅ ተችሏል።
ሮቦቶቹ ራሳቸውን የሚያበዙት ሌሎች ህይወት ያላቸው እንቁራሪቶች በሚራቡበት መንገድ ሳይሆን “ኪነማቲክ” በተባለ የማባዛት ስርዓት እንደሆነም ተመላክቷል።
“ኪነማቲክ” በተባለ የማባዛት ስርዓት የሚፈጠሩት ዜኖቦት ሮቦቶች በሕይወት ቆይተው እና አድገው ልክ እንደ ሌሎች ሮቦቶች ስራ እንዲከውን የሚያስችል ምምርምር እየተካሄደ መሆኑንም ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።