የቻይና ፕሬዝዳንት ዢ የነዳጅ ግብይቱ በዩዋን እንዲሆን የባህረ ሰለጤውን ሀገራት ጠየቁ
ዢ፤ ዩዋንን ለነዳጅ ግብይት ብንጠቀም ዶላር በዓለም ንግድ ላይ ያለውን የበላይነት ማዳከም እንችላለን ብለዋል
ቻይና በባህረ ሰላጤው ላይ እያሳየችው ያለው ተጽዕኖ አሜሪካን አሳስቧታል እየተባለ ነው
የቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ቤጂንግ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ጋር የምታዳርገው የነዳጅ ግብይት በዩዋን እንዲሆን ጠየቁ፡፡
በሳኡዲ አረቢያው ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን አማካኝነት በተዘጋጀው የአረብ ጉባኤ ላይ ንግግር ያሰሙት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ፤ ቤጂንግ ነዳጅና ጋዝን በዩዋን ለምገዛት ትሰራለች ብለዋል፡፡
ዩዋንን እንደ ዋና የነዳጅ መገባበያ መጠቀሙ ቤጂንግ ገንዘቧን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋት ያላትን አላማ የሚደግፍ ከመሆኑ በዘለለ የአሜሪካ ዶላር በዓለም ንግድ ላይ ያለውን የበላይነት የሚያዳክም ነው ሲሉም አክለዋል ፕሬዝዳንቱ።
የቻይናው መሪ ዢ በሪያድ ንግግር ማድረግ የሳኡዲው ልዑል በቀጠናው ያላቸው ተጽእኖ የሚያመላክትና ቻይና ከቀጠናው ጋር ያላትን አጋርነት የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡
የከፍተኛ የነዳጅ ላኪዋ ሳኡዲ አረቢያ እና የግዙፏ የኢኮኖሚ ባለቤት ቻይና መሪዎች ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ለዋሽንግተን ጠንከር ያለ መልእክት ማስተላለፋቸውም ተገልጿል፡፡
መሪዎቹ ዋሽንግተን በተለይም በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ከምታሳየው “ጣልቃ ገብነት” እንድትቆጠብ ማሳሰበቻው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የመሪዎቹ መልእክት ሪያድ ከዋሽንግተን ጋር ያላትን ግንኙነት በሰብአዊ መብት፣ በኢነርጂ ፖሊሲ እና በሩስያ ጉዳይ ላይ ባልተጣጣመበት ወቅት በዚህ ወቅት በመሆኑ ትልቅ ትርጉም አለው ተብሏል፡፡
በተለይም ሳኡዲ አረቢያ በነዳጅ ንግድዋ ዶላርን ለመጣል የምትወስደው እርምጃ ካለ ለዋሽንግተን ትልቅ አደጋ እንደሚሆን ይገመታል፡፡
ቻይና በባህረ ሰላጤው ላይ እያሳየችው ያለው ተጽዕኖ አሜሪካን አሳስቧታል እየተባለ ነው፡፡
በአሁኑ የቻይናው ፕሬዝዳነት ዢ ጉብኝት ወቅት ጥልቅ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ትስስር የተስተዋለበትና በደማቅ አቀባበል ታጀበ መሆን እንዲሁም ፕሬዝዳንቱ ከባህረ ሰላጤው ሀገራትና ጨምሮ አፍሪካ ከሚገኙ የአረብ ሊግ ሀገራት መሪዎች ጋር መገናኘታቸው ለዋሽንግተን ባለስልጣናት የራስ ምታት ሳይሆን እንዳልቀረ እየተነገረ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሪያድከቤጂንግ ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ የመቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳኡድ ሪያድ ከዋሽንግተን ጋር ስላላት ግንኙነት ተጠይቀው ሳዑዲ አረቢያ ቻይናን ጨምሮ ከሁሉም አጋሮቿ ጋር መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል።
"ይህን እንደ ዜሮ ድምር ጨዋታ አንመለከተውም" ያሉት ልዑሉ “በፖላራይዜሽንም ሆነ በመካከላቸው ያለውን ምርጫ አናምንም” ሲሉም አክለዋል፡፡
ምንም እንኳን ሳዑዲ አረቢያ እና ቻይና በርካታ ስትራቴጂካዊ እና ኢኮኖሚያዊ አጋርነት ስምምነቶችን ቢፈራረሙም ግንኙነቱ በአብዛኛው በኃይል ፍላጎት ላይ የተሞረከዘ መሆኑ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡