አዲሱ የሀማስ መሪ ለሊባኖሱ ሄዝቦላ በጻፈው ደብዳቤ ምን አለ?
የሀማስ መሪ ሆኖ የተመረጠው ያህያ ሲንዋር ለመጀመሪያ ጊዜ ለሄዝቦላ መሪ ሰኢድ ሀሰን ነሰረላህ በጻፈው ደብዳቤ ቡድኑ ከእስራኤል ጋር በነበረው ጦርነት ላደረገው ድጋፍ አመስግኗል
ሄዝቦላ በጋዛ ከሚደረገው ጦርነት ጎን ለጎን ለአንድ አመት ያህል በእስራኤል-ሊባኖስ ድንበር አካባቢ የተኩስ ልውውጥ አድርጓል
አዲሱ የሀማስ መሪ ለሊባኖሱ ሄዝቦላ በጻፈው ደብዳቤ ምን አለ?
የሀማስ መሪ ሆኖ የተመረጠው ያህያ ሲንዋር ለመጀመሪያ ጊዜ ለሄዝቦላ መሪ ሰኢድ ሀሰን ነሰረላህ በጻፈው ደብዳቤ ቡድኑ ከእስራኤል ጋር በነበረው ጦርነት ላደረገው ድጋፍ አመስግኗል።
በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላ በጋዛ ከሚደረገው ጦርነት ጎን ለጎን ለአንድ አመት ያህል በእስራኤል-ሊባኖስ ድንበር አካባቢ የተኩስ ልውውጥ አድርጓል። ሄዝቦላ ጥቃቱን የሚፈጽመው ለፍልስጤማውያን አጋርነት ለማሳየት ነው ብሏል።
"የተቀደሰው ተግባራችሁ አጋርነት በመግለጽ፣ በጦርነቱ ድጋፍ በማድረግ እና በመሳተፍ ታይቷል" ሲል ሲንዋ መናገሩን ሮይተርስ የሄዝቦላውን አል ማናር ብሮድካስተር ጠቅሶ ዘግቧል።
ሲንዋር የጋዛው ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ከባለፈው ጥቅምት ወር በአደባባይ ያልታየ ሲሆን ከመሬት ውስጥ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ ሆኖ ጦርነቱን እየመራ ነው ተብሎ ይታሰባል። ሲንዋር ደብዳቤ ልኳል የሚሉ ሪፖርቶች ሲወጡ ይህ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
ሀማስ ባለፈው ማክሰኞ እለት በድጋሚ ለተመረጡት ለአልጀሪያ ፕሬዝደንት አቡዱልመጂድ ተቦኔ የደስታ መልእክት መላኩን ገልጿል።
ሄዝቦላ በኢራን በሚደገፈው 'አክሲስ ኦፎ ሪዚስታንስ' ተብሎ በሚጠራው ቡድን ውስጥ ካሉት ታጣቂ ቡድኖች ውስጥ ከፍተኛ ኃይል ያለው ነው። በጦርነቱ የመጀመሪ ቀናት የቀድሞው የሀማስ መሪ ሄዝቦላ ላደረገው ጣልቃገብነት ማመስገኑ እና ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ መግለጹ ይታወሳል።
ባለፈው አንድ አመት ውስጥ እስራኤል የሄዝቦላን ወታደራዊ አዛዥ ፉአድ ሹክርን ጨምሮ 500 የሄዝቦላ ታጣቂዎችን ገድላለች። ይህ አሀዝ ሄዝቦላ በፈረንጆቹ 2006 ከእስራኤል ጋር ባካሄደው ጦርነት ከደረሰበት ኪሳራ ይበልጣል ተብሏል።
ሄዝቦላ ሲንዋር ተሳትፎበታል የተባለውን የጥቅምቱን ጥቃት እቅድ ቀድሞ እንደማያውቅ ገልጿል። ሲንዋር በዚህ ደብዳቤው ነስረላህ የቀድሞውን የሀማስ መሪ በሀኒየህ ሞት አስመልክቶ ለጻፈለት የማጽናኟ ደብዳቤም ምስጋና አቅርቧል።
የሀማስ የፖለቲካ መሪ የሆነበረው እስማኤል ሀኒየህ እስራኤል ሳታደርሰው አትቀርም በተለባለው ጥቃት ነበር ቴህራን ውስጥ ባረፈበት ክፍል ላይ በተፈጸመ ጥቃት ህይወቱ ያለፈው።
በእስራኤል እና በሊባኖስ ድንበር ላይ ያለው ውጥረት ከሁለቱም በኩል በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ አስገድዷቸዋል።
ውጥረቱ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋትም አለ።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ዮአብ ጋላንት ባለፈው ማክሰኞ እለት የእስራኤል ጦር በጋዛ ያለውን ተልእኮ እያደጠናቀቀ መሆኑን እና ቀጣይ ትኩረቱ ወደ ሊባኖስ ድንበር እንደሚሆን ተናግረዋል።