የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር የአሜሪካን የጦር መርከብ ማጥቃታቸውን ገለጹ
አሜሪካ እና እንግሊዝ የመን ግዛት ውስጥ በሚገኙ የሀውቲ ይዞታዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ለመርከቦች ጥቃት ምላስ እየሰጡ ናቸው።
የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር የአሜሪካን የጦር መርከብ መርከብን ኢላማ ማድረጋቸውን ገልጸዋል
የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር የአሜሪካን የጦር መርከብ ማጥቃታቸውን ገለጹ።
የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር የአሜሪካን የጦር መርከብ እና "ደስቲኒ" የተሰኘች እቃ ጫኝ መርከብን ኢላማ ማድረጋቸውን በዛሬው እለት ገልጸዋል።
ታጣቂዎቹ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ ጥቃት የሚያርሱት ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ አጋርነት ለማሳየት መሆኑን በተደጋጋሚ ይገልጻሉ።
የሀውቲ ጦር ቃል አቀባይ ያህያ ሰርኤ በቴሌቪዥን በተላለፈ መግለጫው ሀውቲዎች "ማይሱን" የተባለችውን የአሜሪካ ዲስትሮየር በቀይ ባህር ላይ ስትጓዝ "በትክክለኛው የናቫል ሚሳይል" አጥቅተዋል።
ሀውቲዎች እቃ ጫን መርከቧን ያጠቁት በፈረንጆቹ ባለፈው ሚያዝያ 20 ወደ እስራኤሉ ኢላት ወደብ በማምራቷ ምክንያት መሆኑን ሰርኤ አክሎ ገልጿል።
ሰርኤ በሁለቱ መርከቦች ላይ ጥቃት የደረሰው መቼ እንደሆነ በትክክል አልገለጸም። ሮይተርስ ሁለት መርከቦች መትተናል የሚለውን የሀውቲዎች መግለጫ ማረጋገጥ እንደማይችል ጠቅሷል።
ለወራት የቀጠለው ሀውቲዎች በቀይ ባህር የሚያደርሱት ጥቃት አለምአቀፉ የንግድ መርከብ እንቅስቃሴ እንዲስተጓጎል፣ የመርከብ ኩባንያዎች በጣም ውድ የሆነውን በደቡብ አፍሪካ ዙሪያ ያለውን መስመር ለመጠቀም እንዲገደዱ እና የሀማስ እና እስራኤል ጦርነት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ይስፋፋል የሚል ፍርሀት እንዲነግስ አድርጓል።
አሜሪካ እና እንግሊዝ የመን ግዛት ውስጥ በሚገኙ የሀውቲ ይዞታዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ለመርከቦች ጥቃት ምላስ እየሰጡ ናቸው።
የሀውቲ ታጣቂዎች የጋዛ ተኩስ አቁም እስከሚደረግ እና በቂ የሰብአዊ እርዳታ መግባቱ እስከሚረጋገጥ ድረስ፣ በተለይ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ባላቸው መርከቦች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት እንደሚቀጥሉበት ግልጽ አድርገዋል።
ሀውቲውች ባደረሱት ጥቃት አንድ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ከዚህ በፊት መስጠሟም ይታወሳል።