እጩ ፕሬዘዳንቶች የመራጮችን 50 በመቶ ካላገኙ ምርጫው ይደገማል
የዛምቢያው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የፕሬዘዳንታዊ ምርጫውን እየመሩ ነው። ዛምቢያ በትናንትናው ዕለት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አካሂዳለች፡፡
የዘንድሮው የዛምቢያ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ በ56 የምርጫ ክልሎች እና በ12 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል።
በደቡባዊ አፍሪካ ክፍል የምትገኘው ዛምቢያ በስልጣን ላይ ያሉት ኤድጋር ሉንጉ በተፎካካሪያቸው ሀኬንዴ ሂችልማ እየተመሩ ይገኛሉ።
የመራጮች ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ትናንት የተጠናቀቀ ሲሆን ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ ደግሞ የምርጫ ውጤት በየምርጫ ጣቢያዎች በመለጠፍ ላይ ይገኛሉ።
የመራጮች ድምጽ ቆጠራ ምርጫው በተካሄደባቸው 156 ምርጫ ክልሎች ውስጥ እስካሁን በ15ቱ የመራጮች ድምጽ ቆጠራው ተጠናቆ ውጤት ይፋ ተደርጓል።
በተካሄዱ የድምጽ ቆጠራ ተቃዋሚው ሀኬንዴ ሂችልማ 171 ሺህ 604 ድምጽ ሲያገኙ በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዘዳነት ኤድጋር ሉንጉ በ110 ሺህ 178 ድምጾች እየተከተሉ መሆኑን የጀርመን ድምጽ የአፍሪካ ከፍል ዘግቧል።