ትራምፕ በድጋሚ ቢመረጡ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መገመት አይቻልም ሲሉ ዘለንስኪ ተናገሩ
ሪፐብሊካንን በመወክል ተስፈኛ ፕሬዝደንት የሆኑት ትራምፕ አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገው ወታደራዊ ድጋፍ በዝቷል ሲሉ በተደጋጋሚ ትችት አቅርበዋል
የአሜሪካ የወካዮች ምክር ቤት ለዩክሬን የ60 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ ማድደቁ ይታወሳል
ትራምፕ በድጋሚ ቢመረጡ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መገመት አይቻልም ሲሉ ዘለንስኪ ተናገሩ።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ዶናልድ ትራምፕ በመጭው ህዳር በድጋሚ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መገመት እንደማይቻል ተናግረዋል።
የዓለም መሪዎች በዚህ ሳምንት ለሚካሄደው የኔቶ ስብሰባ በዋሽንግተን እየተሰበሰቡ ባለበት ወቅት፣ ዘለንስኪ ትራምፕ አሜሪካን የ75 አመት እድሜ ካለው የኔቶ ጥምረት እንደማያስወጡ እና ዩክሬን ሩሲያን ለመከላከል ለምታደርገው ውጊያ የአሜሪካን ድጋፍ እንደሚያስቀጥሉ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።
"(ትራምፕኝ)በደንብ አላውቀውም" ያሉት ዘለንስኪ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከመጀመሯ ከፈንጆቹ የካቲት 2022 በፊት በፕሬዝደንትነታቸው ዘመን "ጥሩ ውይይት" አድርገው እንደነበር አክለው ገልጸዋል።
ትራምፕ "የአሜሪካ ፕሬዝደንት ከሆነ ምን ሊሰራ እንደሚችል ልነግራችሁ አልችልም። አላውቅም።"
ሪፐብሊካንን በመወክል ተስፈኛ ፕሬዝደንት የሆኑት ትራምፕ አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገው ወታደራዊ ድጋፍ በዝቷል ሲሉ በተደጋጋሚ ትችት አቅርበዋል።
የአሜሪካ የወካዮች ምክር ቤት ለዩክሬን የ60 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ ማድደቁ ይታወሳል።
ሁለት የትራምፕ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪዎች ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በመነጋገር ጦርነቱ እንዲቆም ካላደረገች አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም የሚያደርግ እቅድ አቅርበዋል።
ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር ያደረጉት ንግግር በ2019 በፕሬዝደንትነት ዘመናቸው በአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲታገዱ ጥያቄ አስነስቶባቸው ነበር።
በወቅቱ ትራምፕ በጆ ባይደን ላይ በሚያደርጉት የስም ማጥፋት ዘመቻ ዘለንስኪ እንዲረዷቸው ጫና አሳድረውባቸዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር። ነገርግን በ2020 ሴኔቱ ትራምፕን ነጻ አድርጓቸዋል።
ትራምፕ የኔቶ አባል ሆነ በቂ መዋጮ በማያዋጣ ሀገር ላይ ሩሲያ "የፈለገችውን እርምጃ እንድትወስድ" እንደሚያበረታቱ መግለጻቸው አነጋሪ ሆኖ አልፏል።
የኔቶ መተዳደሪያ ደንብ አንዱ የኔቶ አባል ሲጠቃ ሌላው መርዳት እንዳለበት ያስቀምጣል። ዓለም በሙሉ የመጭውን ህዳር ምርጫ እየጠበቀ ነው ያሉት ዘለንስኪ ዩክሬን ለመርዳት የምርጫውን ውጤት መጠበቅ የለባችሁም ሲሉ የአሜሪካ ባለስልጣናትን አሳስበዋል።