የኪየቭ ባለስልጣናት ሰፊ እና ጉልህ የሆነ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ አላደረግንም ብለዋል
ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የዩክሬን ወታደሮችን አወድሰዋል።
የፕሬዝዳንቱ ውዳሴ ሰኞ እለት የሀገሪቱ ጦር በሰሜናዊ ዶኔትስክ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ፉክክር በነበረባት ባክሙት ከተማ አቅራቢያ ወደ ፊት መጓዙን ቀጥሏል ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
"እያንዳንዱን ወታደሮቻችንን አመሰግናለሁ። ሁሉም ተከላካዮቻች ለዛሬው ዜና ሲጠብቁን ቆይተዋል። በባክሙት ውስጥ ያላችሁ ወታደሮች ጥሩ ስራ ሰርታችኋል" በማለት ዘለንስኪ ተናግረዋል።
የዩክሬን የምድር ጦር አዛዥ ኦሌክሳንደር ሲርስኪ እንደተናገሩት ኃይሎቹ በባክሙት አቅራቢያ "ወደ ፊት መጓዛቸውን" ቀጥለዋል።
የሩሲያ ተዋጊዎች እና ባለስልጣናት ለሞስኮ ሁኔታው በጣም አስቸጋሪ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ከጦርነቱ ረጅሙ እና ደም አፋሳሹ በሆነው ውጊያ ሩሲያ ባክሙትን መያዟን ባለፈው ወር መገባደጃ ላይ ገልጻለች።
ዩክሬን ግን ሰራዊቷ አነስተኛ ቦታ እንደያዘ በመግለጽ ሞስኮ ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥራለች መባሉን አስተባብላለች።
ዘለንስኪ እንዳሉት ሩሲያ በዩክሬን ኃይሎች ለሚወስዱት ማንኛውም እርምጃ "ከቁጥጥር ውጭ የሆነ" ምላሽ እየሰጠች ነው።
ሞስኮ "በብቃት፣ በቆራጥነት እና በውጤት" የሚከላከሉ፣ ወራሪዎችን የሚያፈርሱ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ወደፊት የሚሄዱ ሁለት ክፍሎችን ለይታ እርምጃ እየወሰደች ነው ብለዋል።
የሩስያ ጦር ከእሁድ ጀምሮ በምስራቅ ዩክሬን በጦር ኃይሉ ላይ የተሰነዘረውን ሁለት ዋና ዋና የዩክሬይን ጥቃቶች ማክሸፉን ቢገልጽም፤ የኪየቭ ባለስልጣናት ምንም አይነት ሰፊ እና ጉልህ የሆነ አዲስ ዘመቻ አላደረግንም እያሉ ነው።