ምዕራባዊያን መሳሪያዎችን ለዩክሬን ለመላክ ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ የአውሮፓ ወታደራዊ እርዳታ እንዲያፋጥንላቸው ጠየቁ።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ አውሮፓ የዘመናዊ መሳሪያዎችን አቅርቦት እንዲጨምር እና እንዲያፋጥን ጠይቀዋል።
በሩሲያ ላይም ጠንካራ ማዕቀብ እንድትጥልም ዘሌንስኪ አሳስበዋል።
ይህ ካልሆነ ጦርነቱ ለዓመታት ሊራዘም ይችላል ሲሉም ፕሬዚደንቱ አስጠንቅቀዋል።
ዘሌንስኪ ለአውሮፓ ህብረት መሪዎች ባደረጉት ንግግር ሩሲያን አደብ ለማስገዛትና ለመቆጣጠር በ27ቱ ሀገራት እርምጃ ላይ የወደቀ ነው ብለዋል።
ምንም እንኳን የዩክሬን ባለስልጣናት አጋሮቻቸውን የጦር መሳሪያ አቅርቦት እንዲያጠናክሩ ደጋግመው ቢወተውቱም የዘሌንስኪ ጥሪ ባልተለመደ ሁኔታ "ግልጽ የሆነ ብስጭትን" ያሳያል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
"አውሮፓ ሲጠባበቅ ጠላት እንደገና ለመደራጀት እና ለዓመታት ጦርነት ለመዘጋጀት ጊዜ ሊኖረው ይችላል። ይህን መከላከል በእጃችሁ ነው" ብለዋል።
የረዥም እርቀት የጦር መሳሪያዎችን እና ዘመናዊ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ለማቅረብ እንዲሁም የዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባልነትን በተመለከተ ውሳኔዎችን ያዘገየው የአውሮፓ ህብረት ነው ሲሉም አክለዋል።
የምዕራባውያን አጋሮች አዲስ ስሪት መሳሪያዎችን ወደ ዩክሬን መላክ ላይ ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።