በዩክሬን ሙስናና የሀገር ክህደትን አልታገስም- ዘለንስኪ
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሙስናን ለማስወገድ በመልማይ ወታደራዊ ጽ/ቤቶች ላይ ኦዲት ለማድረግ ማቀዳቸውን አስታውቀዋል
የወታደራዊ ምልመላ ባለስልጣን እና ከሩሲያ ጋር በመተባበር የተከሰሱ የፓርላማ አባል መታሰራቸው ይታወሳል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሀገራቸው ከሩሲያ ጥቃት ራሷን የምትከላከልበትን መንገድ ለማግኘት እየታገለች ባለችበት ወቅት ምንም አይነት ሙስና እና በሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ክህደት አልታገስም ብለዋል።
ዘለንስኪ የጸረ-ሙስና ማስጠንቀቂያውን ያሰሙት በወታደራዊ ኃላፊ የጅምላ ዝርፊያና ከሩሲያ ጋር ተባብረዋል የተባሉ የፓርላማ አባል መታሰራቸውን ተከትሎ ነው።
ፕሬዝዳንቱ ባለፈው ወር ሙስናን ለማስወገድ በመልማይ ወታደራዊ ጽ/ቤቶች ላይ ኦዲት ለማድረግ ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።
እርምጃው ለዩክሬን ምዕራባውያን ደጋፊዎች ስር የሰደዱ ወንጀለኞችን ለመታገል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ለማሳየትና መንግስትን ከሙሰኞች የማጽዳት የረጅም ጊዜ ፖሊሲ አካል ነው ተብሏል።
የጦርነቱን ጥረት የሚደግፉ ተራ ዩክሬናውያን በብልሹ አሰራር ተቆጥተዋል ሲሉ ዘለንስኪ ተናግረዋል።
"ለሁሉም የፓርላማ አባላት፣ ባለስልጣናት እና የመንግስት ሰራተኛ ሁሉ ላስጠነቅቅላቸው፤ ማንኛውም ሰው የፓርላማ አባላት፣ ዳኞች፣ ወታደራዊ ባለስልጣናት ወይም ሌሎች ባለስልጣናት መንግስትን በመቃወማችሁ ይቅርታ አይደረግላቸውም" ብለዋል።
ዘለንስኪ ለፓርላማ አባላት ንግግር ሲያደርግ ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባልነትን ለማረጋገጥ የረዥም ጊዜ ዘመቻዋን እንድትጀምር "በግል ጥቅም ምክንያት" ህጉን ለመደገፍ ፈቃደኛ ያልሆኑትን ከአሁን በኋላ አንታገስም ሲሉ አክለዋል።