ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በሰሜንምስራቅ ግንባር ወሳኝ ከተማን እየተከላከሉ ያሉ ወታደሮችን አነጋገሩ
ዩክሬን በሩሲያ የተያዙ በርካታ ቦታዎችን ለማስለቀቅ በፈረንጆቹ 2023 የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ከፍታ የነበረ ቢሆንም ስኬታማ አልሆነችም
ዩክሬን እንደገለጸችው ሩሲያ ከዩክሬኗ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ካርኪቭ በቅርብ ርቀት ያለችውን ኩፒያንስክን ለመያዝ አሁንም እየጣረች ነው
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በሰሜንምስራቅ ግንባር ወሳኝ ከተማን እየተከላከሉ ያሉ ወታደሮችን አነጋገሩ።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በሰሜንምስራቅ ግንባር ከሩሲያ ጋር እየተዋጉ ያሉ ወታደሮችን ማነጋገራቸውን ቢሯቸው አስታውቋል።
ፕሬዝደንቱ ሩሲያ ለወራት ከፍተኛ ጥቃት እየሰነዘረችባት ያለችውን የኩፒያንስክ ከተማን ለመከላከል የተቋቋመውን ኮማንድ ፖስት ጎብኝተዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያወጀውችን ጦርነት ተከትሎ ይዛት የነበረችውን ከተማ ዩክሬን በ2022 መልሳ ተቆጣጥራት ነበር ።
ዩክሬን እንደገለጸችው ሩሲያ ከዩክሬኗ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ካርኪቭ በቅርብ ርቀት ያለችውን ኩፒያንስክን ለመያዝ አሁንም እየጣረች ነው።
ዘለንስኪ በጉብኝታቸው ወቅት ከብርጌዱ አዛዥ ጋር በሚያስፈልገው የመሳሪያ እና የተተኳሽ አቅርቦት ጉዳይ ተወያይተዋል።
ዩክሬን በሩሲያ የተያዙ በርካታ ቦታዎችን ለማስለቀቅ በፈረንጆቹ 2023 የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ከፍታ የነበረ ቢሆንም ስኬታማ አልሆነችም።
በቅርቡ ወታደሮቿ ከበባ ውስጥ መግባታቸውን በመግለጽ ከዶኔስክ ከተማ በቅርብ ርቀት ያለችውን የአቭዲቭካ ከተማን ለቀው እንዲወጡ ማድረጓን መግለጿ ይታወሳል።
ሩሲያ ባለፈው አመት ግንቦት ባክሙትን ከያዘች ወዲህ የአቭዲቭካ መያዝ ትልቅ ድል ነው ተብሏል።