ዘለንስኪ በግንባር ላይ ያሉ የባህር ኃይል አባላትን ጎበኙ
ፕሬዝደንቱ ጉብኝቱን ያካሄዱት የሩሲያን ጥቃት በመከላከል ላሳዩት ሚና ምስጋና ለማቅረብ መሆኑን ተናግረዋል
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በጉዟቸው ለብዙ የባህር ኃይል አባላት ሽልማት አበርክተዋል
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በምስራቅ በኩል በግንባር ላይ የሚገኙ የባህር ኃይል አባላትን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
- ቻይና በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከሞስኮ ጋር ከወገነች 3ኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል ሲሉ ዘለንስኪ አስጠነቀቁ
- ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከወዳጆቻቸው ጋር ለመነጋገር ጃፓን ሂሮሺማ ገቡ
ፕሬዝደንቱ ጉብኝቱን ያካሄዱት የሩሲያን ጥቃት በመከላከል ላሳዩት ሚና ምስጋና ለማቅረብ መሆኑን ተናግረዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለቀቀው ምስል ላይ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በዩክሬን የባህር ኃይል ቀን ወታደራዊ ልብስ ለብሰው ለሴት እና ለወንድ የባህር ኃይል አባላት ሽልማት ሲሰጡ ታይተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ጠንካራ ሲሉ ያሞካሿቸውን የባህር ኃይል አባላት እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
በየቀኑ በሚያወጣው መረጃ ላይ የዩክሬን ጦር እንደገለጸው ወታደሮቹ በምስራቅ ዶንቴስክ በኩል በምትገኘው ማንኪራ ከተማ በኩል የመጡ በርካታ ጥቃቶችን ተከላክለው መልሰዋል ብለዋል።
ባለፈው መስከረም ወር ሩሲያ የራሷ አድርጋ ባካተተችው ዶኔስክ ግዛት ውስጥ ከባድ የሚባሉ ጦርነቶች ተካሂደዋል፤በመካሄድም ላይ ናቸው።
ሩሲያ ዶኔስክን ጨምሮ አራት ግዛቶች በህዝበ ውሳኔ ወደ ሩሲያ መቀላቀሏን ብትገልጽም ዩክሬን እና ምዕራባውያን ሀገራት አልተቀበሉትም።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በጉዟቸው ለብዙ የባህር ኃይል አባላት ሽልማት አበርክተዋል።
ሩሲያ ኔቶ የደህንነት ስጋት እንደደቀነባት በመግለጽ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ልዩ ያለችው ወታደራዊ ዘመቻ 16 ወራትን አስቆጥሯል።