በሱዳን በአንድ ከተማ በተፈጸመ የጎሳ ጥቃት 15ሺ ሰዎች ተገድለዋል-ተመድ
የአሜሪካ መንግሰት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና የሱዳን ጦር የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ ይታወሳል
ከሱዳን ጦር ጋር እየተዋጋ ያለው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከሚያዝያ እስከ ሰኔ በዳርፉር በሚገኙ ማሳሊት በሚባሉት የጎሳ አባላት ላይ ጭፍጨፋ ፈጽሟል የሚል ክስ ቀርቦበታል
በሱዳን በአንድ ከተማ በተፈጸመ የጎሳ ጥቃት 15ሺ ሰዎች መገደላቸውን ተመድ ገለጸ።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና ተባባሪ የአረብ ሚሊሻ በፈጸሙት የጎሳ ወይም የብሔር ጥቃት በሱዳን ዳርፉር ግዛት በምትገኝ አንድ ከተማ ከ10ሺ-15ሺ የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ ተመድን ሪፖርት ጠቅሶ ዘግቧል።
ለተመድ የጸጥታው ምክርቤት የቀረበው ሪፖርት እንደሚያመለክተው በሱዳን ጦርነቱ ከተጀመረበት ከሚያዝያ 2023 ወዲህ በአል ጀኒና 12ሺ ገደማ ሰዎች ተገድለዋል።
ከሱዳን ጦር ጋር እየተዋጋ ያለው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከሚያዝያ እስከ ሰኔ በዳርፉር በሚገኙ ማሳሊት በሚባሉት የጎሳ አባላት ላይ ጭፍጨፋ ፈጽሟል የሚል ክስ ቀርቦበታል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቀደም ሲል የቀረበበትን ክስ ማስተባበሉ እና ማንኛውም ወታደር በመብት ጥሰት ተሳትፎ ከተገኘ እርምጃ እንደሚወስድ መናገሩ ይታወሳል።
ለተመድ የጸጥታው ምክርቤት የቀረበው ሪፖርት ጥቃቱ "የታቀደ፣ የተቀነባበረ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና በተባባሪ የአረብ ሚሊሻዎች" የተፈጸመ መሆኑን ጠቅሷል።
የማሳሊት ጎሳዎች በደረሰባቸው ጥቃት አል ጀኒናን በእግራቸው ወደ ጎረቤት ሀገር ቻድ በብዙ ቁጥር ተሰደዋል።
በደረሰባቸው ጥቃት አል ጀኒናን ግዛት ከመልቀቃቸው በፊት የማሳሊት ጎሳዎች በግዛቷ አብላጫ ቁጦር ነበራቸው።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኬላዎች ላይ ዝርፍያ እና ግድያ ሲፈጽሙባቸው ነበር ተብሏል።
የአሜሪካ መንግሰት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና የሱዳን ጦር የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ ይታወሳል።
የሱዳን ጦርም በአሜሪካ የቀረበውን ክስ አይቀበልም።