የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማገት የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው
የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማገት የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው
የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማገት የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች የሽብር ክስ እንደተመሰረተባቸው ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ህዳር ወር ከደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወጥተው ወደ ቤተሰቦቻቸው እየሄዱ ሳሉ ነበር ታግተው እስካሁን ደብዛቸው የጠፋው፡፡
እንደዘገባው በማገት ወንጀል ተጠርጥረው በዛሬው እለት የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ከሊፋ አብዱረሂማን በሚል የክስ መዝገብ ስር ያሉ17 ግለሰቦች ናቸው፡፡
ክሳቸውም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ዛሬ ተደምጧል ተብሏል፡፡
መንግስት ለእገታው በኦሮሚያ ክልል እየተንቀሳቀሰ ነው የሚባለውን በጃል መሮ የሚመራውን ኦነግ ሽኔን ከሷል፡፡ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ከዋሉት 9 ሰዎች ክሳቸው የተሰማው የ7ቱ ተጠርጣሪዎች ሲሆን ሌሎቹ 2ቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ክሳቸውን አላዳመጡም፡፡ ቀሪዎቹ ተጠርጣሪዎች በመፈለግ ላይ ናቸው፡፡
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የታገቱ ተማሪዎች በተመለከተ ከተወካዮች ምክርቤት አባል ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፣ መንግስት ተማሪዎቹን ለማግኘት የሚችለውን ሁሉ እያደረገ መሆኑንና የታጋች ተማሪዎቹ ዶክመንት መገኘቱን ገልጸው ነበር፡፡