ትምህርት በሰሜን ኢትዮጵያ
በሰሜን ኢትዮጵያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል
ከ22 ሺህ በላይ መምህራንም ለሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ደመወዝ አልተከፈላቸውም ብሏል የህጻናት አድን ድርጅት
በሰሜን ኢትዮጵያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል አለ ትኩረቱን በህጻናት ላይ በማድረግ የሚታወቀው የህጻናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን)።
ድርጅቱ ለአል ዐይን በላከው መግለጫ እንዳለው በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ውጪ እንደሆኑ የዚሁ ተቋም ሪፖርት ያስረዳል።
ከ22 ሺህ በላይ መምህራን ላለፉት ሁለት ዓመት እና ከዛ በላይ ደመወዝ አልተከፈላቸውም ተብሏል።
በሰሜን ኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦