በኦሮሚያ ክልል ማንነትን መሰረት ያደረግ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ የፈጸሙ አካላት መደምሰሳቸውን ክልሉ አስታወቀ
በኦሮሚያ ክልል ማንነትን መሰረት ያደረግ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ የፈጸሙ አካላት መደምሰሳቸውን ክልሉ አስታወቀ
በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ወለጋ ዞን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ማንነት ላይ በማነጣጠር ግድያ ከፈጸሙት 24ቱ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዘግቧል፡፡
የኦሮሚያ ክልል በወቅቱ ግድያውን የሽብር ጥቃታ ያለው ሲሆን 32 ሰዎች መገደላቸውንም አስታውቆ ነበር፡፡ ነገርግን የሞቱት ሰዎች ቁጥር 54 እንደሆኑ ከስፍራው ምንጭ አግኝቻለሁ ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ግድያው “በሶስት ቀበሌዎች ላይ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ያነጣጠረ” ነበር፤ ሊወገዝ ይገባዋል ማለቱም ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ማንነትን መሰረት ባደረግው ግድያ ማዘናቸውንና አጥቂዎች ለመቅጣት ሰራዊት ማሰማራታቸውን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነርን ጠቅሶ ኢዜአ እንዘገበው “በኦነግ ሸኔ የአጥፊ ቡድን ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን እና በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተከናወነ” መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ እንደተናገሩት ዘግናኝ የግድያ ጥቃትና የንብረት መውደም ባደረሱ የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላት የክልል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል።
ኢሰመኮ የፌደራልና የክልል መንግስታት በግድያው ላይ በአፋጣኝ ምርመራ እንዲጀምሩና፣ ለጥቃት ተጋላጭ መሆኑ ለረጅም ጊዜ ከሚታወቀው ቦታ ሰራዊቱ እንዲወጣ የተደረገበት የጀርባ ምክንያት እንዲታወቅና የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡