እስራኤል 2ሺህ ቤተእስራኤላዊያን ከኢትዮጵያ ለመውሰድ አቅዳ ነበር
እስራኤል 2 ሺህ ቤተ እስራኤላዊያንን ከኢትዮጵያ ለመውሰድ ባስቀመጠችው እቅድ መሰረት ዛሬ 300 የሚሆኑ ቤተ እስራኤላዊያን እየሩሳሌም ከተማ መድረሳቸውን ጅዊስ ኒውስ በድረገጹ ዘግቧል።
የእስራኤል የስደተኞች ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ፒና ታማኖ ሻታ ቤተ እስራኤላዊያኑ ቤን ጉሪዮን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ዛሬ እስራኤል ከገቡት ቤተ እስራኤላዊያን ውስጥ አብዛኞቹ አድሜያቸው ከ24 ዓመት በታች እንደሆኑ ተገልጿል።
ወደ እስራኤል ይወሰዳሉ ከተባሉት 2 ሺህ ዜጎች መካከል 893 ያህሉ ህጻናት እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን ተጨማሪ ቤተ እስራኤላዊያን በቀጣይ ወደ አስራኤል ለማምጣት እንደሚሰራም ሚኒስትሯ በአቀባበል ስነ ሰርአቱ ላይ ተገልጿል።
ዛሬ እየሩሳሌም የደረሱት እነዚህ ቤተ እስራኤላዊያን በቀጥታ ከኤርፖርት ወደ ተዘጋጀላቸው ኳራንቲን ማዕከል የተወሰዱ ሲሆን ከ14 ቀናት በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚቀላቀሉን ተጠቁሟል።