32 አይነት ስፖርታዊ ውድድሮች የሚካሄድበት ትልቁ አለማቀፍ ስፖርታዊ መድረክ እስከ ነሃሴ 5 2016 ይቀጥላል
የ128 አመታት እድሜ ያለው የኦሎምፒክ ውድድር በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ትናንት ምሽት በድመቀት ተከፍቷል።
ከዚህ ቀደሞቹ የኦሎምፒክ መድረኮች ለየት ባለ መልኩ በተከፈተው የፓሪስ ኦሎምፒክ አትሌቶች የየሀገራቸውን ሰንደቅ ይዘው በጀልባዎች ተጉዘዋል።
100 ጀልባዎች አትሌቶችን አሳፍረው በታዋቂዎቹ ኖትረዳም እና ሉቭረ በኩል አልፈዋል።
6 ኪሎሜትር የሚረዝመው ደማቅ የጀልባ ጉዞ በኤፍል ታወር ተጠናቆም የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በይፋ የፓሪስ ኦሎምፒክ መከፈቱን አብስረዋል።
እስከ ነሃሴ 5 2016 ዓም በሚቆየው ውድድር ዙሪያ ቁጥሮች ምን ይላሉ? ተከታዩን ምስል ይመልከቱ፦