100 የሚጠጉ ጀልባዎች የየሀገራቱን አትሌቶችን አሳፍረው በሴን ባህር በመቅዘፍ በኖትረዳም እና ሉቭረ በኩል አልፈዋል
የፈረንሳይ መዲና ከ100 አመት በኋላ በድጋሚ ያስተናገደችውንን ኦሎምፒክ መክፈቻ ከስታዲየም ውጭ በልዩ መልኩ አካሂዳለች።
100 የሚጠጉ ጀልባዎች የየሀገራቱን አትሌቶችን አሳፍረው በሴን ባህር በመቅዘፍ በኖትረዳም እና ሉቭረ በኩል አልፈዋል።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልኡክም በጀልባ በመሆን በሴን ባህር በመቅዘፍ በኖትረዳም እና ሉቭረ በኩል አልፈዋል።
6 ኪሎሜትር የሚረዝመው ደማቅ የጀልባ ጉዞ በኤፍል ታወር ሲጠናቀቅም ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በይፋ የፓሪስ ኦሎምፒክ መከፈቱን አብስረዋል።
ደማቅ የመክፈቻ ስነስርአቱ ለአራት ስአታት የቆየ ሲሆን፤ በመጨረሻም ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ በተንሳፋፊ ፊኛ የኦሎምፒክ ችቦ ተለክሷል።