በፓሪስ ኦሎምፒክ የእንቁላል እና ስጋ እጥረት አጋጠመ
ፈረንሳይ በበኩሏ እጥረቱ ያጋጠመው ፍላጎቱ ከጠበቅነው በላይ በመሆኑ ነው ብላለች

የፓሪስ ኦሎምፒክ ነገ ይጀመራል
በፓሪስ ኦሎምፒክ የእንቁላል እና ስጋ እጥረት አጋጠመ፡፡
በየአራት ዓመቱ አንዴ የሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር የዘንድሮው በፓሪስ አስተናጋጅነት ሊጀመር አንድ ቀን ብቻ ቀርቶታል፡፡
ለውድድሩ ወደ ስፍራው ያቀኑ አትሌቶች በዛሬው ዕለት ወደ ኦሎምፒክ መንደር የገቡ ሲሆን የእንቁላል እጥረት እንዳጋጠማቸው ለብዙሃን መገናኛዎች ተናግረዋል፡፡
ከእንቁላል በተጨማሪም የተጠበሰ ስጋ እጠረት መኖሩን የፈረንሳዩ ለኪፕ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
የፓሪስ ኦሎምፒክ ምግብ አቅራቢ ኩባንያ ሃላፊ ሳዶክሶ እንቁላል እና ስጋ እጥረት ማጋጠሙን አምነው ችግሩ የተፈጠረው ፍላጎቱ ከፍተኛ በመሆኑ ነው ይታረማል ብለዋል፡፡
የኦሎምፒክ መንደር 13 ሚሊዮን ምግብ ለማቅረብ በእቅድ የተያዘ ሲሆን በየዕለቱ ደግሞ 40 ሺህ ምግቦች ለአትሌቶች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
በኦሎምፒክ መንደሩ ውስጥ ከ208 ሀገራት የተውጣጡ 13 ሺህ አትሌቶች እንደሚገቡ ይገመታል፡፡
ለቀጣዮቹ 15 ቀናትም በየዕለቱ የሚቀርበው 40 ሺህ ምግብ 10 የዓለም ዋንጫዎች ለይ የሚቀርበውን ያክል ተመሳሳይ ነው ተብሏል፡፡
ታዋቂዋ ሙዚቀኛ ሲሊንዲዮን በኦሎምፒክ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ለምታቀርበው አንድ ሙዚቃ ሁለት ሚሊየን ዶላር ሊከፈላት ነው
ለአትሌቶች ምግብ የሚያቀርቡት ድርጅቶች የእስያ፣ ፈረንሳይ፣አፍሪካ-ካሪቢያ እና የዓለም ጣዕም ያላቸው ምግቦችን ያቀርባሉ፡፡
ለተወዳዳሪዎች የሚቀርቡት ምግቦች ውስጥ ወተት ስጋ እና እንቁላል የግድ ከፈረንሳይ ገበሬዎች የሚመረቱ መሆን አለባቸው የተባለ ሲሆን ቀሪዎቹን ከ ሌሎች ሀገራት የሚገቡ ናቸው፡፡
በኦሎምፒክ መንደር ውስጥ 200 የውሃ፣ ጭማቂዎች እና ለስላሳ መጠጦች በየቦታው የተዘጋጁ ሲሆን መጠጫዎቹ ሁሉም ዳግም ጥቅም ላይ ከሚውሉ ቁሳቁሶች የተመረቱ ናቸው፡፡