ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” መክፈቷን ተከትሎ በሩሲያ እና በአውሮፓ መካከል ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ ገብቷል
አራት የአውሮፓ ሀገራት 43 የሩሲያ ዲፕሎማቶች በስለላ ወንጅል ከጠረጠሯቸው በኋላ አባረዋል፡፡
ቤልጂየም ለ21 የሩስያ ዲፕሎማቶች ለብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ናቸው ብላ መናገሯን እና የሁለት ሳምንት ጊዜ መስጠቷን ሲጂቴን ዘግቧል፡፡
የቤልጂየም ጎረቤት ኔዘርላንድስ በዲፕሎማሲያዊ ቪዛ በሀገሪቱ ውስጥ የነበሩትን 17 ሩሲያውያንን ማባረሯን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአየርላንድ ሪፐብሊክም አራት "ከፍተኛ ባለስልጣናት" ግዛቷን ለቀው እንዲወጡ ጠይቃለች፤ ነገር ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የተባረረበትን ምክንያት ግልጽ አላደረገም፡፡ቼቺያም አንድ ዲፕሎማት ከሀገሯ እንዲወጡ 72 ሰአታት ብቻ ሰጥታለች።
በፕራግ የሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ያለውን የሩሲያ የስለላ መረጃ እየቀነስን ነው" ብሏል። ዲፕሎማቶቹን ያረሩት አራቱም ሀገራት የአውሮፓ ህብረት አባል ናቸው፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” መክፈቷን ተከትሎ በሩሲያ እና በአውሮፓ መካከል ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ ገብቷል፡፡
ሩሲያ ወደ ግጭት የገባቸውም የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ ሶቬት አባል ሀገራት እየተስፋፋ ነው ይህም ለደህንነቴ ያሰጋኛል በሚል ነበር፡፡ ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ግጭት ውስጥ ከገቡ በኋላ ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉንም አይነት ማእቀብ ጥለዋል፤እየጣሉም ነው፡፡
ሁለቱ ሀገራት ግጭቱን በሰላም ለመፍታት ድርድር ጀምረዋል፡፡