ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት 50 ሰዎች ተገደሉ
በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቁ ፎቶዎች በአቧራ እና በፍርስራሽ የተሸፈኑ የበርካታ ወጣቶች አስከሬኖችን እና ከጀርባቸው በከፊል የተጎዳ ህንጻ ያሳያሉ
"ሩሲያ ለዚህ ጥቃት በእርግጠኝነት ኃላፊነት ትወስዳለች" ሲሉ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ተናግረዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት 50 ሰዎች ተገደሉ።
ሩሲያ በማዕከላዊ ዩክሬን ፖልታቫ በሚገኘው ወታራዊ ኢንስቲትዩት ላይ በፈጸመችው የሚሳይል ጥቃት ቢያንስ 50 ሰዎች ሲገደሉ እና ሌሎች 271 የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።
ይህ ጥቃት በዚህ አመት ከተፈጸሙት የአንድ ጊዜ ጥቃቶች ውስጥ እጅግ ከባዱ ነውም ተብሏል።
በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቁ ፎቶዎች በአቧራ እና በፍርስራሽ የተሸፈኑ የበርካታ ወጣቶች አስከሬኖችን እና ከጀርባቸው በከፊል የተጎዳ ህንጻ ያሳያሉ።
"ሩሲያ ለዚህ ጥቃት በእርግጠኝነት ኃላፊነት ትወስዳለች" ሲሉ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በቴሌግራም ገጻቸው ተናግረዋል።
ጥቃቱ በወታደራዊ ኮሙኒኬሽን ኢንስቲትዩት ላይ ገዳት ማድረሱን የገለጹት ዘለንስኪ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ አዘዋል። ዘለንስኪ ምሽት ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት የሟቾቹን ቁጥር ወደ 51 ከፍ አድርገዋቸዋል።
"ከወደመዉ ህንጻ ፍርስራሽ ስር ሰዎች መኖራቸው ይታወሳል" ብለዋል ዘለንስኪ። "ህይወት ለማዳን የሚቻለንን ሁሉ እየሰራን ነው"
የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 50 ነው ብሏል።
የፖልታቫ ግዛት አስተዳዳሪ ፍሊፕ ፕሮኒን እንደተናገሩት 15 ሰዎች ከፍርስራሹ ስር ሊኖሩ ይችላሉ። የዩክሬን የምድር ኃይል እንደገለጸው ወታደሮች ተገድለዋል።
በጥቃቱ የተገደሉት ወታደሮች ምን ያህል እንደሆኑ ባይገልጹም፣ ጠንካራውን ወታደራዊ ኃይል ያለውን ጠላቷን ለመመከት ጥረት እያደረገች ላለችው ዩክሬን ግን ትልቅ ኪሳራ ሆኖ ተመዝግቧል።
"የዩክሬን የምድር ኃይል እዝ በኢንስቲትዩቱ የነበሩ ወታደሮችን ህይወት ለመከላከል በቂ ጥንቃቄ ስለመደረጉ ምርመራ እየተደገ ነው" ብሏል የምድር ኃይሉ ያወጣው መግለጫ።
ሩሲያ 2 1/2 አመታ ባስቆጠረው ጦርነት፣ በዩክሬን ላይ እያደረሰች ያለውን የሚሳይል አና የድሮን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች። ባለፈው ሳምንት ሩሲያ በኪቭ እና በሌሎች ከተሞች ላይ ከባድ የሚባል የአየር ጥቃት አድርሳለች። ዩክሬንም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኙ የነዳጅ ማጣሪያ የኃይል ጣቢዎች ላይ በ158 ድሮኖች ጥቃት አድርሳለች።
ዩክሬን የሩሲያ ኃይል ለማዛባት ድንበር ጥሳ በሩሲያ ላይ ጥቃት የከፈተች ቢሆንም ሩሲያ ጥቃቷን በማጠናከር ወደፊት እየገፋች ነው።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ምዕራባውያን አጋሮቻቸው የአየር መካከያ እንዲሰጧቸው እና የረጅም ርቀት ሚሳይሎቻቸውን በሩሲያ ግዛት ውስጥ ኢላማ ለመምታት እንዲጠቁሙ እንዲፈቅዱላቸው ጥሪ አቅርበዋል።