52 ግብጻውያን የኮሮና ምርመራ ውጤት ሳይዙ አዲስ አበባ ገቡ
ግብጻውያኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ለ14 ቀናት ያህል ቆይተው ወደ ኩዌት ለመሄድ ነው ተብሏል
ግብጻውያኑ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲቆዩ መደረጋቸውን የአዲስ አበባው የግብጽ ኢምባሲ አስታወቀ
ግብጻውያኑ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲቆዩ መደረጋቸውን የአዲስ አበባው የግብጽ ኢምባሲ አስታወቀ
የኮሮና ምርመራ ውጤት ሳይዙ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ግብጻውያን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲቆዩ መደረጉን በአዲስ አበባ የግብፅ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያወጣችው መመሪያ ማንኛውም ከውጭ ሚመጣ ዜጋ ኢትዮጵያ ከመድረሱ ከሶስት ቀን በፊት ተመርምሮ ነጻ የሚል የምስክር ወረቀት መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
ኤምባሲው ድርጊቱ እንደተሰማ የግብፅ ቆንስል እና አንድ የኤምባሲው ዲፕሎማት ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሄዳቸው እና ግብጻውያኑ አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውን ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡
በአውሮፕላን ማረፊያው ግብጻውያኑን እና የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናትን ማነጋገሩን ኤምባሲው ገልጿል፡፡ ኤምባሲው የጉዳዩን እውነታ ለማጣራት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርንና በካይሮ ያለውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቢሮን ማነጋገሩን አስታውቋል፡፡
ኤምባሲው እስካሁን ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ያደረገው ግንኙነት እንደሚያመለክተው የግብፅ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ለ14 ቀናት ያህል ቆይተው ወደ ኩዌት ለመሄድ እንደሆነ ገልጿል፡፡
ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ለጉብኝት ሳይሆን ከካይሮ ባገኙት ቪዛ ወደ ኩዌት ለመሄድ ቢሆንም እነዚሁ ዜጎች ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የተቀመጠውን የኳራንቲን መመሪያው የጣሱ መሆናቸውን ኤምባሲው አረጋግጧል፡፡
ኤምባሲው በአሁኑ ሰዓት የእነዚህን ዜጎች መብቶች እንዳልተጣሱና አያያዛቸው ሕግን የጠበቀ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች ከኤምባሲው ጋር በመተባበር 52 ግብጻውያን በአዲስ አበባ በሚገኙ ሆቴሎች እንዲያርፉ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም በአዲ አበባ የሚገኘው የግብጽ ኤምባሲ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ግብጻውያን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ የጤና ሕጎችን በሙሉ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ከኢትዮጵያ በኩል መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡