ፖለቲካ
የአውሮፓ ሀገራት ዜጎቻው በዩክሬን ጦርነት ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ ጥሪ አቀረቡ
ለዜጎቻቸው ጥሪ ካቀረቡ 7 ሀገራተ ውስጥ ፈረንሳይ ጀርመንና ጣሊያን ይገኙበታል
አበዛኞቹ ከአውሮፓ ሀገራት የተውጣቱ 20 ሺህ ሰዎች በፍቃዳቸው ለዩክሬን ተስልፈው እየተዋጉ ነው
ሰባት የአውሮፓ ሀገራት ዜጎቻቸው በበጎ ፈቃደኝነት ለዩክሬን ተሰልፈው ሩሲያን አንዳይዋጉ ጥሪ ማስተላለፋቸው ተሰምቷል።
ዜጎቻውን ለዩክሬን ተሰልፋችሁ አንዳትዋጉ ካሉ ሀገራ መካከልም ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን እና ሰፔን እንደሚገኙበት ነው የተገለፀው።
የሀገራቱ የፍትህ ሚኒስትሮች በጋራ ካካሄዱት ጉባዔ በኋላ የአውሮፓ ሀገራት ዜጎች በፈቃደኝት ለዩክሬን ተሰልፈው እንዳይዋጉ የሚከለክለውን ህግ በሙሉ ድምጽ ያፀደቁት ተብሏል።
በጉባዔው ላይ የተሳተፉ “የቨንደም ቡድን” በመባል የሚጠሩት የፈረንሳይ፣ የኔዘርላንድስ፣ የጣሊያን፣ የስፔን፣ የሉአንብርግ እና የቤልጂየ የፍትህ ሚኒስትሮች ናቸው።
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሊድሜር ዘለንስኪ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ባሳለፍነው የካቲት ወር ላይ በጎ ፈቃደኛ ተዋጊዎች ለዩክሬን ተሰልፈው እንዲዋጉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት መግለጫም፤ አበዛኞቹ ከአውሮፓ ሀገራት የተውጣቱ 20 ሺህ ሰዎች በራሳቸው ፍላጎት ለዩክሬን መሰለፋቸውን አረጋግጠዋል።