ከሰሞኑ በሶማሌ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ህገወጥ ነው በሚል የተወሰዱ ገንዘቦች ለባለቤቶቹ ተመለሱ
ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች ህገ ወጥ ነው በሚል የአርብቶ አደሩ ገንዘብ መያዙ ውዝግብ ፈጥሮ እንደነበር ተገልጿል
“አዳዲሶቹ የብር ኖቶች ለዘመናት ተዘንግቶ የነበረውን የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ውክልና ያረጋገጡ ናቸው” አቶ ሙስጠፌ
ከሰሞኑ በሶማሌ ክልል አንዳንድ የአርብቶአደሮች አካባቢዎች ህገወጥ ነው በሚል የተወሰዱ ገንዘቦች ለባለቤቶቹ ተመለሱ
ከብር ኖት ለውጥ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ከአንዳንድ የሶማሌ ክልል አርብቶአደሮች አካባቢዎች ህገወጥ ነው በሚል ተወሰደው የነበሩ ገንዘቦች ለባለቤቶቹ መመለሱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ አስታወቁ።
ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች ህገ ወጥ ነው በሚል የአርብቶ አደሩ ገንዘብ መያዙ ውዝግብ መፍጠሩን የገለፁት ምክትል ፕሬዘዳንቱ ምን ያህል ገንዘብ እንደተያዘ እና ለባለቤቶቹ ተመላሽ እንደተረገ ግን አልገጹም፡፡
ሆኖም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅጅጋ ቅርንጫፍ በመገኝት የአዳዲሶቹን የብር ኖት መቀየር ስነስርዓት አስጀምረዋል።
በስነ ስርዓቱ አዳዲሶቹ የብር ኖቶች ለዘመናት ተዘንግቶ የነበረውን የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ውክልና ያረጋገጡ ናቸው ያሉት አቶ ሙስጠፌ በአዲሱ የ10 ብር ኖት ላይ የተቀመጠው የግመል ምስል ለዘመናት ለተገፋው የአርብቶ አደር የህብረተሰብ ክፍል ተስፋን የሰጠ ነው ሲሉ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
የፀጥታ ኃይሎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ ወጥነት መያዝ እንደሌለባቸው በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና በብሄራዊ ባንክ ገዥው ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ትናንት መገለጹ የሚታወስ ነው።