አቶ ልደቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከእስር እንዲፈታቸው ፍርድ ቤት አዘዘ
ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ ዋስትናቸው ተከብሮ ከእስር እንዲለቀቁ ቢያዝም የቢሾፍቱ ፖሊስ ሊፈታቸው አልቻለም
አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል የምስክሮች ቃል ተሰምቷል
አቶ ልደቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከእስር እንዲፈታቸው ፍርድ ቤት አዘዘ
አቶ ልደቱ አያሌው በተሰጣቸው ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ጥቅምት 05 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው በተከሰሱበት ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ሶስት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የምስክር ቃላቸው ተሰምቷል፡፡
ፍርድ ቤቱም የሰማውን ምስክርነት መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
አቶ ልደቱ የተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትናን ተከትሎ ለምን እንዳልተፈቱ የጠየቀ ሲሆን የቢሾፍቱ ፖሊስ ሃላፊ ቀርቦ እንዲያብራራ የታዘዘውን ትዕዛዝም ፍርድ ቤቱ ተመልክቷል። ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ ዋስትናቸው ተከብሮ ከእስር እንዲለቀቁ በተደጋጋሚ ትዕዛዝ ቢሰጥም የቢሾፍቱ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አክብሮ እስካሁንም ሊፈታቸው አልቻለም፡፡
ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረትም የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ተቀይሯል መባሉን ተከትሎ ተወካይ ወይም የክፍል ሃላፊ በቀጣይ ቀጠሮ ቀርበው እንዲያብራሩም ትዕዛዝ ሰጥቷል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡
በህገወጥ ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ክስ በተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትና መሰረት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከእስር እንዲፈታቸውም ፍርድ ቤቱ አዟል።