አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ “የሀገርን ውለታ ክደዋል”ያላቸውን የቀድሞ ተመራቂዎቹን ዲግሪ ሊነጥቅ እንደሚችል አስጠነቀቀ
አአዩ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የአቋም መግለጫ አውጥቷል
ዩኒቨርስቲው “ከሽብርተኞች ጋር ሲተባበሩ ተደርሶባቸዋል”ያላቸው ጥቂት የቀድሞ ተመራቂዎቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አስጠንቅቋል
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሀገርን ውለታ ክደዋል ባላቸው የቀድሞ ተመራቂዎቹ ላይ ዲግሪያቸውን እስከመንጠቅ የደረሰ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አስጠነቀቀ፡፡
በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩት የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት በዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት በፕ/ር ጣሰው ወልደሃና የተነበበ መግለጫ ማውጣታቸውን ዩኒቨርስቲው በይፋዊ የማህበረሰብ ትስስር ገጾቹ አስታውቋል፡፡
ዩኒቨርስቲው ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የእውቀትን በር በመክፈት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ “ባለውለታ ” መሆኑን የሚያትተው መግለጫው አያሌ የቀድሞ ተመራቂዎቹ በመላው ዓለም የሽብር ቡድኑን ድርጊት በማውገዝ ምዕራባዊያን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማሳሰባቸውን ገልጿል፡፡
በአንድ ቀን ውጊያ ብዙ ድል ተግኝቷል፤ ድሉ ነገም ይቀጥላል- ጠ/ሚ ዐቢይ
ሆኖም ይህን የዩኒቨርሲቲውን የሀገር ውለታ “ክደዋል”ያላቸው ጥቂት ግለሰቦች ደግሞ “ከሀገር አፍራሽ ሽብርተኞች ጋር ሲተባበሩ በሀገር ላይ ክህደት በመፈፀም በሚስጥር ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል” ብሏል፡፡
“ተደርሶባቸዋል” ያላቸው እነዚሁ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያስጠነቀቀም ሲሆን “ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ዲግሪያቸውን እስከመንጠቅ የሚደርስ ህጋዊ እርምጃ” እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡
የሽግግር መንግሥት እንመሠርታለን በሚል በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዘ
የዩኒቨርሲቲው የቀድሞም ይሁን የአሁን ምሁራን “የጀመሩትን ሀገርን የማዳን ትግል” እንደሚደግፍ አውቀው “እስከመጨረሻው እንዲፋለሙ”ም ጥሪ አቅርቧል፡፡
የዩኒቨርስቲው የማህበረሰብ አባላት በመግለጫው የውጭ ጫናን በማውገዝ “እኛም ከፊትም ከኋላም ተሰልፈን መሪያችንን ተከትለን እስከ ግንባር ድረስ እንዘምታለን” ብለዋል፡፡