የብልጽግና ፓርቲ ዛሬ ማምሻውን አመራሩን መርጧል
የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።
እየተካሄደ ያለው የብልጽግና ፓርቲ ዛሬ ማምሻውን አመራሩን መርጠዋል።
በዚህም የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት ምርጫ ዛሬ ተካሂዷል።
በውጤቱም
1ኛ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በ1480 ድምፅ የፓርቲው ፕሬዝዳንት
2ኛ አቶ አደም ፋራህ በ1330 ድምፅ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት
3ኛ ደመቀ መኮንን በ970 ድምፅ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
ብልፅግና ፓርቲ አንድ ፕሬዝዳንት እና ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቴች እንደሚኖሩት የፓርቲው የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ አስታውቀዋል።