ፍርድ ቤቱ በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል
ባለፈው መጋቢት በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ ያወጣው ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ማነው?
ፍርድ ቤቱ የጦር ወንጀሎችን፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን፣ የዘር ማጥፋት ወንጀልን እና የጥቃት ወንጀሎችን ለፍርድ ለማቅረብ በፈረንጆች 2002 ተቋቁሟል።
በአባል ሀገራት ዜጎች ወይም በአባል ሀገራት ግዛት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን በመመርመር ክስ ማቅረብ ይችላል። 123 አባል ሀገራት ያሉት ሲሆን፤ የ2023 በጀቱ 170 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ ነው።