እሌኒ ገብረመድህን ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት አባልነታቸው ተነሱ
የምጣኔ ሃብት ባለሙያዋ ከሰሞኑ በዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል የተዘጋጀ ነው በተባለና በበይነ መረብ በተካሄደ ስብስባ እንደተሳተፉ መገለጹ ይታወሳል
እሌኒ ከምክር ቤቱ አባልነት የተነሱት “መንግስት የመለወጥና የሽግግር መንግስት የማቋቋም አላማ ባለው ስብሰባ ላይ ባራመዱት ጠንካራ አቋም” ነው ተብሏል
እሌኒ ገብረመድህን (ዶ/ር) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተሰየመው ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት አባልነታቸው ተነሱ፡፡
ዶ/ር እሌኒ ዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል በተባለ ተቋም ከሰሞኑ ተዘጋጅቶ በነበረና “በድብቅ በተካሄደ” የበይነ መረብ ስብስባ ላይ በመሳተፋቸው ነው ከአባልነት የተነሱት፡፡
በአንድ ቀን ውጊያ ብዙ ድል ተግኝቷል፤ ድሉ ነገም ይቀጥላል- ጠ/ሚ ዐቢይ
በስብሰባው ላይ ያነሷቸው ሐሳቦች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀን ቡድን በግልጽ የሚደግፍ ሆኖ ተገኝቷል ያለው አማካሪ ምክር ቤቱ “በሕጋዊ ምርጫ ቅቡልነት ያገኘውን የኢፌዴሪ መንግስት የመለወጥና የሽግግር መንግስት የማቋቋም አጀንዳ ላይ በመሳተፍ ሐሳቦችን ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል” ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ የማሸነፍ አቅም ተደራጅቶ እና ተጠናክሮ እየወጣ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎቹ ምንም እንኳን በግል የራሳቸው የፖለቲካ አመለካከት ሊኖራቸው ቢችልም፤ የአማካሪነት ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ከየትኛውም ፓርቲም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ነጻ መሆን እንደሚገባቸዉ ህገ ደንባችን በግልጽ ያስቀምጣል ያለው አማካሪ ምክር ቤቱ ትናንት ቅዳሜ ኅዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባን አድርጓል፡፡
በስብሰባው ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን “በምርጫ ስልጣን የያዘን መንግስት የመለወጥና የሽግግር መንግስት የማቋቋም አላማ ባለው ስብሰባ ላይ ባራመዱት ጠንካራ አቋም”በጣም ማዘኑን በመግለጽ፣ ግለሰቧ የአማካሪ ምክር ቤቱ አባል ሆነው መቀጠል እንደማይችሉ ያሳለፈውን ውሳኔ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ከዛሬ ከኅዳር 19 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት መነሳታቸውንም ምክር ቤቱ ገልጿል፡፡
አስራ ስድስት አባላት ያሉት ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤቱ ከታህሳስ 5/2013 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሰየሙ ይታወሳል፡፡
ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን ከነዚህ አማካሪዎች መካከል አንዷ ናቸው፡፡