ግብጽ የ2036 እና የ2040 ኦሎምፒኮችን ለማስተናገድ ጥያቄ እንደምታቀርብ ተገለጸ
ከግብጽ በተጨማሪ የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታውንም ለማስተናገድ ልትጠይቅ እንደምትችል ይጠበቃል
በአረቡ አለም ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ግብጽ ለስፖርት መሰረተልማት ግንባታ የስፖርት በርካታ ቢሊዮን ዶላሮችን እያፈሰሰች ነው
ግብጽ የ2036 እና የ2040 ኦሎምፒኮችን ለማስተናገድ ጥያቄ እንደምታቀርብ ተገለጸ።
ግብጽ የ2036 እና የ2040 ኦሎምፒክ ጨዋታቸውን ለማስተናገድ ጥያቄ እንደምታቀርብ የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ኃላፊ ተናገሩ።
የግብጽ የመሰረትልማት እና የስፖርት ቦታዎች ግንባታ እድገት እያሳየ ስለሆነ ግብጽ የ2036ቱን እና የ2040ውን ኦሎምፒክ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ጥያቄ እንደምታቀርብ የአፍሪካ ናሸኛል ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር(ኤኤንኦሲኤ) ኃላፊ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
አህጉሪቱ በታሪኳ የኦሎምፒክ ጨዋታ አስተናግዳ አታውቅም። ካይሮ የ2008ቱን የኦሎምፒክ ጨዋታ ለማስናገድ ያደረገችው ጥረት አይሳካላት ቀርቷል።
በአረቡ አለም ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ግብጽ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን፣ ስቴዲየሞችን እና የስፖርት ህንጻዎችን ለመገንባት በርካታ ቢሊዮን ዶላሮችን እያፈሰሰች ነው።
ግብጽ ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ በምስራቅ ካይሮ እየገነባችው ባለችው አዲስ የአስተዳደር ከተማ ውስጥ የሚገኘው አለምአቀፍ የኦሎምፒክ መንደር 93ሺ ህዝብ መያዝ የሚችል ስቴዲየም እና ሌሎች 21 የስፖርት መሰረተ ልማቶች እንደሚኖሩት ይጠበቃል።
የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ኃላፊ ሙስጠፋ በራፍ በፖሪስ ኦሎምፒክ መዝጊያ ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት "ግብጽ የ2036 እና የ2040" ኦሎምፒክ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት ጥያቄ ታቀርባለች።
ከግብጽ በተጨማሪ የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታውንም ለማስተናገድ ልትጠይቅ እንደምትችል ይጠቃል።
"አፍሪካ ጨዋታ የማስተናገድ እድል አላት። የ2040ውን የማስተናገድ እድሏ ከፍ ያለ ነው" ብለዋል የአለምአቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የሆኑት በራፍ።
"መንገድ እና አየርማረፊያ የመሳሰሉትን አይነት መሰረተልማቶች ማየት አለብን። ግብጽ(ኦሎምፒክን ) ማስናገድ የሚችል የመሰረተልማት አቅም አላት።"
የአሜሪካዋ ሎስአንጀለስ የ2028ቱን የክረምት ኦሎምፒክ የምታስተናግድ ሲሆን የአውስትራሊያዋ ብርዝባኔ ደግሞ የ2032ቱን ኦሎምፒክ ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ ነች።
ኢንዶኔዥያ፣ ቱርክ፣ኳታር እና ሳኡዲ አረቢያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት እና ከተሞች የ2036 ኦሎምፒክ ለማዘጋጀት ፍላጎት ማሳየታቸውን የአለምአቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት ቶማስ ባች ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።