የሳዑዲው አልናስር የማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያን ለማስፈረም እንደሚፈለግ አስታወቀ
የክርስቲያኖ ሮናልዶ ክለብ አል ናስር ለዴቪድ ዴሂያ 272 ሺህ ዶላር ሳምንታዊ ደመወዝ አቅርቦለታል
የ32 ዓመቱ ግብ ጠባቂ የማንቸስተር ዩናይትድ የኮንትራቱ በፈረንጆቹ ሀምሌ 1 2023 ተጠናቋል
የሳዑዲ አረቢያ ፕሮ ሊግ ተሳታፊ አልናስር የእግር ኳስ ክለብ የማቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያን ለማስፈረም እያማተረ መሆኑ ተሰምቷል።
የክርስቲያኖ ሮናልዶ ክለብ በሆነው የሳዑዲ አረቢያ ፕሮ ሊግ ተሳታፊ አልናስር የእግር ኳስ ክለብ ለስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያ 272 ሺህ ዶላር (250 ሺህ ዩሮ) ሳምንታዊ ደመወዝ ማቅረቡም ተሰምቷል።
የ32 ዓመቱ ግብ ጠባቂ የማንቸስተር ዩናይትድ ቆይታ ኮንትራቱ በፈረንጆቹ ሀምሌ 1 2023 መጠናቀቁም የሚታወስ ነው።
በሰርግ እረፍት ላይ የሚገኘው ዴሂያ እስካሁን ድረስ ከክለቡ ጋር በኮንትራት ውል እድሳት ዙሪያ ምንም አይነት ንግግር አለመጀመሩም ተገልጿል።
የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ የኢንተር ሚላኑ ግብ ጠባቂ አንድሬይ ኦናናን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው የተባለ ሲሆን፤ ይህም የዴቪድ ዴሂያን ስንብት እውን ሊያደርገው ይችላል ተብሏል።
ስፔናዊው ግብ ጠባቂ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ በአስራ ሰባት ጨዋታዎች ላይ መረቡን ሳያስደፍር መውጣቱን ተከትሎ የወርቅ ጓንት ማሸነፉ ይታወቃል።
ለማንቸስተር ዩናትድ 545 ጨዋታዎች ላይ የተሳተፈው የ32 ዓመቱ ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያ፤ በፈረንጆቹ በ2013 ከማንቸስተር ዩናትድ ጋር የፕሪምየር ሊግ ወንጫን ማንሳትም ችሏል።