አልጄሪያ የአረብ ሊግ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የያዘውን አቋም ለማስተካከል እንደምትሰራ አስታወቀች
የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን እና የግብፅ ጉዳይ ነው- ቡሩንዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ም/ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ውይይቱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከ5 የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
በዚህም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአልጄሪያ፣ ቡሩንዲ፣ ቤኒን፣ ኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መምከራቸውን ጠቅሰዋል።
እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ አቶ ደመቀ ከአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታን ላማምራ ጋር ባደረጉት ውይይት አረብ ሊግ የያዘውን የተሳሳተ አቋም እንዲያስተካክል አልጄሪያ እንድታግዝ ጠይቀዋል፡፡
አልጄሪያ ቀጣይ የአረብ ሊግ ሊቀመንበር ነች፡፡
ኢትዮጵያ በአረብ ሊግ ላይ ያላትን ቅሬታ በኢትዮጵያ ለሚገኙት የአልጀሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጸች
ይህን ተከትሎ አልጄሪያ፤ ሊጉ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የያዘውን የተሳሳተ አቋም ለማስተካከል እንደምትሰራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ራምታን ላማምራ አስታውቀዋል፡፡
የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በውይይት እንዲፈታ አልጄሪያ እንደትምደግፍም ላማምራ አክለው ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቡሩንዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር አልበርት ሺንጊሮ ጋርም ተወያይተዋል።
አምባሳደር አልበርት በውይይቱ ሃገራቸው የታላቁ የህዳሴ ግድብ በአፍሪካዊያን መፍትሄ እንዲያገኝ መሰራቱን እንደምትደግፍ ገልጸዋል እንደ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጻ።
ግብጻዊው አቡል ጌት የአረብ ሊግ ዋና ጸሐፊ ሆነው በድጋሚ ተመረጡ
አቶ ደመቀ መኮንን ከላይቤሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባካደር ዲ ማክስዌል ሳህ ማያህ ጋር የተወያዩም ሲሆን፤ በዚህም የላይቤሪያ መንግስት ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆም ማረጋገጡን አስታውቀዋል።
ግብፅ፤ ቱርክ ለኢትዮጵያ የመሳሪያ ሽያጭ እንዳታከናውን ስለመጠየቋ ጥያቄ የቀረበላቸው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ “መሳሪያ ገዛን አልገዛንም መብታችን ነው፤ ይህንን ያለው ሀገር መሳሪያ የሚገዛው እኛን አስፈቅዶ አይደለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።