የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማስጠበቅ ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ መግባባት መፍጠር የግድ ይላል- አሜሪካ
የሰኔ 14 ምርጫ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ነጻና ፍትሃዊ ባልሆነበት ሁኔታ ነው የተካሄደው
በምርጫው የመምረጥ መብታቸውን የተጠቀሙ ኢትዮጵያውያንን እንደምታደንቅም አሜሪካ አስታወቃለች
የሰኔ 14ቱ ምርጫ ኢትዮጵያ ከፍተኛ አለመረጋጋት ውስጥ ባለችበት እና የምርጫው ሂደት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ነጻና ፍትሃዊ ባልሆነበት ሁኔታ መካሄዱን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ፣ ምርጫው ታዋቂ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ከምርጫው አለመሳተፋቸካገለሉበት፣ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች በታሰሩበት እና በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ግጭት ባለበት ሁኔታ መካሄዱን ገልጿል።
የሃገሪቱን ሉዕላዊነት፣ አንድነትና ህገ- መንግስታዊ ስርዕት ለማስጠበቅ ሁሉን- አቀፍ ጥረት በማድረግ ብሄራዊ መግባባት ላይ መድረስ የግድ እንደሚልም ነው የጠቆመው።
በዚህ የድህረ ምርጫ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ መሪዎች ሁከትን እንዳይቀበሉ ሌሎችን ወደግጭት የሚያነሳሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡም ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
"በትግራይ ክልል የቀጠለው ግጭት እና ሰብዓዊ ቀውስ አፋጣኝ ተግባራዊ እርምጃ የሚጠይቅ ነው" ሲልም ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመልክቷል።
በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት ፤የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ እንዲወጣ፣ የተፈፀሙ ከፍተኛ ወንጀሎች እንዲመረመሩና ለሰብዕዊ እርዳታ ያልተገደበ መንገድ እንዲከፈትም ጠይቋል።