አሜሪካ በግድቡ ላይ የራሷን አቋም አንጸባረቀች
ድርድሩን ለመታዘብ የገባችው አሜሪካ የግድቡ ሙከራና ውሃ ሙሌት ያለስምምነት መጀመር የለበትም የሚል አቋም አንጸባረቀች
አሜረካ የግድቡ ሙከራና የውሃ ሙሌት ያለስምምነት መጀመር የለበትም የሚል አቋም ያዘች
አሜሪካ የግድቡ ሙከራና የውሃ ሙሌት ያለስምምነት መጀመር የለበትም የሚል አቋም ያዘች
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ባወጣው መግለጫ አሜሪካ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ሙከራና የውሃ ሙሌት ያለስምምነት መጀመር የለበትም የሚል አቋም አንጸባርቃለች፡፡
አሜሪካ የግድቡ ድርድር ታዛቢ ሆና ብትገባም አሁን ላይ የራሷን አቋም እያንጸባረቀች ትገኛለች፡፡
አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ2015 የኢትዮጵያ፣የሱዳንና ግብፅ መሪዎች በሱዳን የፈረሙት ዲክላሬሽን ኦፍ ፕሪንሲፕልስ በተለይም በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት አለማድረስ ከሚለው ስምምነት ጋር አብሮ መሄድ ስላለበት ነው ብላለች፡፡
“ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚገኙ ህዝቦች በግድቡ አስተዳደር ደህንነት ላይ የሚያነሱትን ስጋት እንረዳለን፤ እናም አለም አቀፍ ደረጃ የሚያሟሉ ሁሉንም አይነት የደህንነት ጥንቃቄዎች ማድረግ ይገባል ” በማለት አቋም ይዛለች፡፡
ግብፅ ስምምነቱን ለመፈረም ያሳየችውን ተነሳሽነት ያደነቀችው አሜሪካ ኢትዮጵያም የጀመረችውን ብሄራዊ ውይይት በተቻለ ፍጥነት ጨርሳ ስምምነቱን እንድትፈርም ትጠበቃለች ብላለች፡፡
ከዚህ በጨማሪምአሜሪካ ሶስቱ ሀገራት ስምምነቱን እስኪፈርሙ ድረስ ጥረቷ እንደሚቀጥል ገልፃለች፡፡
በቅርቡ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በአሜሪካ እያካሄዱት ያለውን ድርድር ሊቋጭ የሚችል የመጨረሻ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ኢትዮጵያ ከህዝብ ጋር ውይይት ያስፈልገኛል በማለት ወደ አሜሪካ ሳትሄድ ቀርታለች፡፡