አቶ ዮሀንስ “የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ” ፕሬዘዳንትነት ሹመትን አልቀበልም አሉ
አቶ ዮሀንስ “የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ” ፕሬዘዳንትነት ሹመትን አልቀበልም አሉ
አቶ ዮሀንስ ቧያለው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዘዳንትንት ሹመትን እንደማይቀበሉት ከአማራ መገናኛ ብዙሀን ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታውቀዋል፡፡
የአማራን ህዝብ ጥቅም ለማስከበር በየትኛውም ደረጃ እንደሚሰሩ የተናገሩት አቶ ዮሀንስ የመለስ ዜናዊ አካዳሚ ፕሬዘዳንትነት ሹመትን ግን እንደማይቀበሉ ገልጸዋል፡፡
“ራሴን ሳዳምጠው፤ስመረምረው በዛ ተቋም መስራት ቢኖርብኝም አንኳን፣ አሁን ባለው ብራንድ [ስም]“ መስራት የምችልበት ሁኔታ የለም” ያሉት አቶ ዮሀንስ የተለየ ቦታ ቢመደቡ ወይንም አካዳሚው የተለየ ብራንድ [ስም] ከተሰጠው ማገልገል እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ዮሀንስ ከብልጽግና ፓርቲ መመስረት በፊት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዋና ጸሀፊ በመሆን እያገለገሉ የነበሩ ናቸው፡፡
ሰሞኑን የአማራ ክልል ምክርቤት ባካሄደው አስቸካይ ስብሰባ አቶ ዮሀንሰ ወደ ፌደራል መንግስት መሄድ የለባቸውም የሚል ሰፊ ክርክር ከምክርቤት አባላቱ ተነስቶ ነበር፡፡
በወቅቱ አዳዲስ ሹመቶችን ያቀረቡት የአማራ ክልል ርእስ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ ዮሀንስም ሆኑ ሎሌች ክልል ላይ የነበሩ አመራሮች ወደ ፌዴራል የስራ ኃላፊነት የሚሾሙት በፓረቲ ዉሳኔና በራሳቸው ፈቃድ መሆኑን መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
አቶ ዮሀንስ በክልሉ በአዲስ የተሸሙ አመራሮች ሹመትን ግን አልተቃወሙም፡፡