ግድቡ በኢትዮጵያ ምድር፣በኢትዮጵያዊ ውሃ፣ በራሷ የውሃ ድርሻ የሚገነባ ነው
የአሜሪካ መግለጫ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው- ፈቂ አህመድ
በውሃ ጉዳዮች ላይ የ30 ዓመታት ልምድ ያላቸው አቶ ፈቂ አህመድ ነጋሽ ህዳሴ ግድብን የተመለከተው የአሜሪካ መግለጫ በግልጽ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው ብለዋል፡፡
ወትሮውኑ አሜሪካ በጉዳዩ ልትገባ አይገባም ነበር ያሉት አቶ ፈቂ በታዛቢነትና አሸማጋይነት ሾልካ ገብታ የነበረችው ሃገር አደራዳሪ እና የጉዳዩ አካል ከመሆንም አልፋ ስምምነቱን እስከማዘጋጀት እስከምትደርስ ድረስ ዝም መባል እንዳልነበረበት ነው የተናገሩት፡፡
”ግብጽ እና ሱዳን ተስማምተዋል፤ግብጽ ኢትዮጵያን ለመጫን እየሞከረች ነው ይህ ደግሞ ድርድሩ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው” ብለዋል፡፡
“3ኛ ወገን መግባት አልነበረበትም፤ የአሜሪካ መግለጫም እንደ አንድ ውሃ ጉዳዮች ላይ ለረዥም ጊዜ እንደሰራ ባለሙያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ” ነው ያሉት፡፡
ግድቡ “በኢትዮጵያ ምድር፣በኢትዮጵያዊ ውሃ፣ በራሷ የውሃ ድርሻ የሚገነባ በመሆኑ አሁንም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትኛውንም ዋጋ ከፍሎ አንድ መሆን” እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡