የአውሮፓ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚልክ አስታወቀ
የአውሮፓ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚልክ አስታወቀ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአውሮፓ ሕብረት የውጪ ጉዳይ እና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ እና ከሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦሬል ጋር ዛሬ ማለዳ ተወያይተዋል።
በውይይቱ ሃገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸውላቸዋል፡
ህብረቱ ጅምሩን ሃገራዊ የለውጥ አጀንዳ እንደሚደግፍ የገለጹ ጆሴፍ ቦሬል በበኩላቸው መጪው ሃገራዊ ምርጫ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲና መረጋጋት ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም ህብረቱ የምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚልክ ማስታወቃቸውን በግል ትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በህብረቱ ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ትናንት በአፍሪካ-አውሮፓ ህብረት የኮሚሽን ለኮሚሽን ተቋማዊ የግንኙነት ጉባዔ ላይ መሳተፉ የሚታወስ ነው፡፡
በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የአሜሪካ መንግስት የልማት ተራድኦ ድርጅት (USAID) ለመጪው ምርጫ የሚደረገውን ድጋፍ አስመልቶ ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2012 ዓ.ም የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
በስምምነቱ መሰረትም USAID የ30 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር እገዛ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡