በዩክሬን በጦርነት ላይ የሚሞቱ የአሜሪካ ተዋጊዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ
በዩክሬን ጦር ግንባር ከ20 በላይ አሜሪካውያን ደብዛቸው እንደጠፋ ተነግሯል
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት አዳዲስ ክስተቶችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።
በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ላይ እየሞቱ ያሉ ቅጥረኛ የአሜሪካ ተዋጊዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ።
በጦርነቱ ላይ ከዩክሬን ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ያሉ የአሜሪካ የአሜሪካ ተዋጊዎች በየጊዜው ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ተነግሯል።
በተለይም ባለፉት ስድስት ወራት በጦርነቱ የሚጎዱ አሜሪካውያን ቁጥር በእጥፍ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፤ ከ20 በላይ አሜሪካውያን ደብዛቸው እንደጠፋም ሲኤንኤን ባደረኩት ምርመራ ደርሼበታለሁ ብሏል።
አሜሪካውያኑ የተለያየ የስራ ድረሻ በመያዝ በዪክሬን ጦር ውስጥ እየተዋጉ እያሉ በሩሲያ ጥቃት መገደላቸው ነው የተነገረው።
ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ አሜሪካውያን ተዋጊዎች በምስራቅ ዩክሬን ፖክሮቭስክ ክልል ውስጥ ድልድይ የማፈንዳት ተልእኮ ላይ እያሉ በሩሲያ ድሮን መገደላቸው ነው የተነገረው።
በፈቃዳቸው ለዩክሬን እየተዋጉ ካሉ አሜሪካውያን መካከል ባለፉት 6 ወራት ከተገደሉት ውስጥ የ5 ተዋጊዎችን አስክሬን እስካሁን ከጦር ሜዳ በማንሳት ለቤተሰቦቻቸው መላክ እንዳልተቻለም ነው የተገለጸው።
የጠፉ አሜሪካውያን ዘመዶች ልጆቻቸውን አስክሬን አግኝተው መቅበር ባለመቻላቸው እንዲሁም የሚወዷቸውን ሰዎች መሞታቸው በይፋ መግለጽ አለመቻሉን እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።
ከተጀመረ 1 ሺህ 72ኛ ቀኑን የያዘው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት አዳዲስ ክስተቶችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም ከምርጫ ቅስቀሳ ጀምሮ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
ሩሲያ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመነጋገር እና ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት ፈቃደኛ መሆኗን አስታውቃለች።
ዩክሬን በበኩሏ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲደረግ እየጠየቀች ትገኛለች።
የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ኔቶ በበኩሉ ዩክሬን አሁን ላይ ለድርድር ዝግጁ አለመሆኗን እና አውሮፓ ለኪቭ ተጨማሪ ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።