ኦስካር ጀንኪን ከሁለት ወር በፊት ነበር በሩሲያ ጦር የተማረከው
አውስትራሊያ ለዩክሬን ሲዋጋ በሩሲያ የተማረከው ዜጋዋ ደህንነት ያሳስበኛል አለች።
አራተኛ ዓመቱን ሊይዝ ጥቂት ወራት የቀረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት አዳዲስ ክስተቶችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።
ሁለቱም ሀገራት ጦርነቱን ለማጠናቀቅ የተለያዩ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ ሲሆን ቅጥረኛ ወታደሮችን መመልመል አንዱ ዘዴ ነው።
ዩክሬን ከቀጠረቻቸው ቅጥረኛ ወታደሮች መካከልም የአውስትራሊያ ዜግነት ያለው ኦስካር ጀንኪስንስ አንዱ ነው።
ይህ ቅጥረኛ ወታደር ከሁለት ወር በፊት በሩሲያ ጦር የተማረከ ሲሆን ከተማረከ በኋላ የት እንደተገደለ ሲገለጽ ቆይቷል።
አውስትራልያ የዜጋዋ ደህንነት እንደሚያሳስባት የገለጸች ሲሆን ሩሲያም ምላሽ ሰጥታለች።
ሩሲያ እንደገለጸችው ኦስካር ለዩክሬን ሲዋጋ ከሁለት ወር በፊት መመማረኩን እና ደህንነቱ ተጠብቆ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቃለች።
የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔኒ ዎንግ ኦስካር በህይወት እንዳለ ከሩሲያ ማረጋገጫ የደረሳቸው ቢሆንም አሁንም የዜጋችን ደህንነት ያሳስበናል ብለዋል።
ሩሲያ ዜጋችንን በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ደህንነቱን እንድትጠብቅ ሲሉም ሚንስትሩ አሳስበዋል።
አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም ከምርጫ ቅስቀሳ ጀምሮ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
ሩሲያ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመነጋገር እና ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት ፈቃደኛ መሆኗን አስታውቃለች።
ዩክሬን በበኩሏ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲደረግ እየጠየቀች ትገኛለች።
የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ኔቶ በበኩሉ ዩክሬን አሁን ላይ ለድርድር ዝግጁ አለመሆኗን እና አውሮፓ ለኪቭ ተጨማሪ ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።