![](https://cdn.al-ain.com/images/2020/1/13/223-182418-whatsapp-image-2020-01-13-at-05.47.12_700x400.jpeg)
የዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ በሱዳን ጉብኝት አያደረጉ ነው
የዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አንዋር ቢን መሀመድ ጋርጋሽ በሱዳን ካርቱም ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
የሱዳን የመረጃ ምንጮች ለ አል-አይን እንዳረጋገጡት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ጋርጋሽ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሀሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡
የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሀን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብደላህ ሀምዱክ የሀገሪቱን ወቅታዊ ጉዳይ ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚኒስትር ዴኤታው ጋር ይወያያሉ ተብሏል፡፡
ዶ/ር ጋርጋሽ ከሉዓላዊው ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ጄነራል ሙሀመድ ሀምዳን ዳግሎ እና ከሱዳኑ አቻቸው አል-ሲዲቅ አብዱላዚዝ እና ሌሎች ባለስልጣናት ጋርም በተከታታይ ተገናኝተው ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡