አስትራዘኔካ የኮቪድ-19 ክትባትን ከመላው አለም ሊሰበስብ መሆኑን አስታወቀ
ኩባንያው ክትባቱን ለመሰብሰብ ያመለከተው ከሁለት ወራት በፊት ቢሆንም ተቀባይነት ያገኘው ግን በትናንትናው እለት ነው
አስትራዘኔካ ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ የተሻሻሉ ክትባቶች በብዛት በመኖራቸው ምክንያት በመላው አለም ያለውን ክትባቱን ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታውቋል
አስትራዘኔካ የኮቪድ-19 ክትባትን ከመላው አለም ሊሰበስብ መሆኑን አስታወቀ።
ግዙፉ የኮቪድ-19 ክትባት አምራች ኩባንያ አስትራዘኔካ ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ የተሻሻሉ ክትባቶች በብዛት በመኖራቸው ምክንያት በመላው አለም ያለውን ክትባቱን ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታውቋል።
ኩባንያው የቬክስቪሪያ ክትባቱን ከአውሮፖ ገበያ ለማስወጣት የጀመረውን እንቅስቃሴ እንደሚገፋበት ገልጿል።
"ብዙ እና የተለያዩ አይነቶች የኮቪድ ክትባቶች እየተመረቱ ስለሆነ አሁን ላይ ገበያው በተሻሻሉ ክትባቶች ተሞልቷል" ያለው ኩባንያው ይህ የቬክስቪሪያ ክትባት ፍላጎት እንዲቀንስ አድርጎታል ሲል አክሎ ገልጿል።
ኩባንያው ክትባት ማምረቱን እና ማሰራጨቱን አቁሟል።
ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የአንግሎ-ስዊዲሽ የሆነው ይህ የመድሃኒት ኩባንያ የሚያመርተው ክትባት የመደም መርጋት እና የደም ፕላትሌቶች መቀነስ የመሳሰሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ያስከትል በሚል ምክንያት ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር።
ኩባንያው ክትባቱን ለመሰብሰብ ያመለከተው ከሁለት ወራት በፊት ቢሆንም ተቀባይነት ያገኘው ግን በትናንትናው እለት ነው።
የኮቪድ ክትባት ፍላጎት መቀነስ በእድገቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረበት ኩባንያው ለመተንፈሻ አካል ቫይረስ የሚሆኑ ክትባቶችን እና የውፍረት መድሃኒቶችን ወደማምረት ተሸጋግሯል።