ታጣቂው ጥቃቱን ካደረሰ በኃላ ራሱን ማጥፋቱ ተነግሯል
በማዕከላዊ ሩሲያ በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ አንድ ታጣቂ በከፈተዉ ተኩስ 13 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ።
በኢዜቨስክ ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ በታጣቂ በተፈፀመው ጥቃት ከሞቱት 13 ሰዎች መካከል ስድስቱ ህጻት መሆናቸውንም የአካባቢው ፖሎስ አስታውቋል።
በተጫሪም በጥቃቱ ህጻናትን ጨምሮ 21 ሰዎች መቁሰላቸውን ሩሲያን ቱዴይ ይዞት በወጣው ዘገባ አመላክቷል።
ጥቃቱን የፈፀመው ታጣቂ በሁለት ሽጉጥ ጥቃቱን ማድረሱ የተገለፀ ሲሆን፤ የናዚ አርማ ያለበት ቲሸርት ለብሶ እንደነበረም ተነግሯል።
ታጣቂው ጥቃቱን ከፈፀመ በኋላ በያዘው መሳሪያ ራሱን ማጥፋቱንም ፖሊስ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ጥቃቱ መፈጸሙን የሩሲያ የሀገር ውስጥ ጉዳይም በቴሌግራም ገጹ ላይ አረጋግጧል።
እንደዚህ አይነት ጥቃቶች በሩሲያ ያልተለመዱ መሆኑን ተከትሎ ጥቃት ፈጻሚውን ምን እንዳነሳሳው ለማወቅ አዳጋች አንደሚያደርገው ተነግሯል።
የሩሲያ ፐሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጥቃቱ ማዘናቸውንም መግለጻቸውን ከሬምሊን አስታውቋል።
ኢዜቨስክ ትምህርት ቤት ወደ 650,000 የሚጠጉ ነዋሪዎች ባሏት ኢዝሄቭስክ ከተማ መሃል ላይ የሚገኝ ሲሆን ለማዕከላዊ የመንግስት ሕንፃዎች አቅራቢያ ነዉ ተብሏል።
በትምህር ቤቱ ውስጥ እድመያቸው ከስድስት እስከ 17 መካከል የሚገኙ ወደ 1,000 የሚጠጉ ተማሪዎች እና 80 የሚሆኑ መምህራን እንዳሉ ተነግሯል።